top of page
  • Writer's pictureየመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ

"ገንዘብ ሳይከፍሉ ለሰዎች ሊያበረክቱ የሚችሉዋቸው ስጦታዎች"



"ገንዘብ ሳይከፍሉ ለሰዎች ሊያበረክቱ የሚችሉዋቸው ስጦታዎች"

“ትልቅ ነገር ማድረግ ቢያቅተን ከፍቅር ጋር ትንሽ ነገር ማድረግ አያቅተንም” ይላሉ ማዘር ተሬዛ።

ተዕለትዕለት ውሎአችን ዋጋ (ገንዘብ)የማያስከፍሉ፤ ነገር ግን ለሰዎች እጅግ ዋጋ ያላቸውን ነገሮችን አንድ ያልታወቁ ጸሐፊ እንዲህ አስቀምጠዋቸዋል::

የመስማት ስጦታ

ሰዎች ስለጉዳያቸው ወይም ስለችግራቸው ሲያወጉ ከልብ መስማትን የመሰለ ስጦታ የለም:: ታዲያ ሳናቋርጣቸው፤

በሃሳብ ሌላ ቦታ ሳንሔድ ወይም ስለምንመልስላቸው መልስ ሳናሰላሰል መሆን አለበት:: ዝምብሎ ከልብ ማዳመጥ ብቻ!

ፍቅር የማሳየት ስጦታ

ፍጹም ሳይሰስቱ ከልብ ሰዎችን በመጨበጥና በማቀፍ ለእነርሱ ያለዎትን ፍቅር፤ ትኩረትና አድናቆት ይግለጹላቸው::

የሳቅ ስጦታ

በየዕለቱ የሚገጥምዎትን አስደሳች ሁኔታዎች (ጽሑፎች፤ ፎቶዎች፤ ካርቱኖች) በመላክ ደስታዎን (ሳቅዎን) ለሰዎች ያካፍሉ፤ የሌሎችንም ደስታ ወይም ሳቅ እንዲሁ ይካፈሉ::

የጽሑፍ ስጦታ

ሰዎች ስላደረጉልዎ መልካም ነገር ምስጋናዎን በራስዎ የእጅ ጽሑፍ በመጻፍ ይስጧቸው፤ የዚህ ዓይነትጽሑፎች ዘመን ከመሻገራቸውም በላይ ሕይወት ይቀይራሉ::

የምስጋና ስጦታ

ሰዎች ለሠሩት ሥራ ወይም ላደረጉት ለውጥ ትልቅ ሥራ ሠርተሻል፣ ዛሬ በጣም አምሮብሃል፣ በጣም ቆንጆ ምግብ ሠርተሻል እና ወዘተ.. በማለት አድናቆትዎን ይግለጹ ይህን ዓይነት እውነተኛ አድናቆት የሰዎችን ቀን ብሩህ ያደርጋል:: መልካም ውለታ የማድረግ ስጦታ ከዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎ ወጣ ይበሉና ለሚወዱዋቸው ሰዎች ያልተጠበቀ ድርጊት በመፈጸም ያስደንቋቸው::

አረጋውያንን መጠየቅ፤ ሕፃናትን ማጫወት ወዘተ…

የሰላም ስጦታ

ሰዎች ብቻቸውን መሆን በሚፈልጉበት ሰዓት ብቻቸውን እንዲሆኑ በመፍቀድ (በመተው) ሰላማቸውን እንደስጦታ ይስጧቸው::

የበጎ ቃላት ስጦታ

መልካም ሰላምታ በመስጠት፤ ለተደረገልዎ ነገር ሁሉ ምስጋና በማቅረብ በመልካም ቃላትዎ የሰዎችን መልካም ስሜት

ይጠብቁላቸው::


98 views0 comments

Recent Posts

See All
bottom of page