top of page
  • Writer's pictureየመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ

በአድዋ ተራራዎች ላይ የአንባገነኑ መሪ የቤኒቶ ሙሶሊኒ የፊት ቅርፅ ሐውልት ቆሞ እንደነበር.ያውቁ ኖሯል.....?


በአድዋ ተራራዎች ላይ የአንባገነኑ መሪ የቤኒቶ ሙሶሊኒ የፊት ቅርፅ ሐውልት ቆሞ እንደነበር.ያውቁ ኖሯል.....?

ይህን ያውቁ ኖሯል.....?

በአድዋ ተራራዎች ላይ የአንባገነኑ መሪ የቤኒቶ ሙሶሊኒ የፊት ቅርፅ ሐውልት ቆሞ እንደነበር......በ 2ተኛ የኢጣሊያን ወረራ ዘመን በአድዋ በሱሎዳ ተራራ ፊት ለፊት ላይ በፋሺስት ወታደሮች የተገነባው ይህ ሃውልት ቁመቱ 4.80 ሜትር ከፍታ የነበረው ሲሆን ፤  የጣሊያን ወታደሮች በወቅቱ የዚህ ሐውልት በቦታው የመገንባታቸው ዋንኛው ዓላማ እና ለማስተላለፍ የፈለጉት መልዕክት:-

በ1888ዓ.ም ላይ የደረሰባቸውን ሽንፈት በውስጣቸው ለነበረው ቁጭት እና እፍረት ማካካሻ ይሆናል ብለው በማሰብ እንዲሁም በሃጉረ አፍሪካ ለነበሩት ለሌሎቹ የቀኝ ገዢዎች የአውሮፓውያን ሃገራት የጠንካራነት ማሳያ የሞራል ማበረታቻ ምልክት ይሆናል በማለት ነበር ከ40 ዓመት በፊት ሽንፈታቸው ከተጎነጩባት ቦታ ላይ በወርሃ የካቲት 1928 ዓ.ም ላይ ገንብተው ያቆሙት። ሆኖም ግን አሁን ሐውልቱ በቦታው የለም ሀገራችን ከፋሺስት ጣሊያን ነፃ ከሆነች በኋላ በቦታው ምንም አይነት የሐውልቱ አሻራ እና ፍርስራሽ እንዳይኖር ተደርጎ ሊፈረስ ችሏል።


ክብርና ሞገስ ከወራሪ ነፃ ሀገር ላስረከቡን ጀግኖች አርበኞቻችን


ምንጭ - አዲስ አድማስ

10 views0 comments
bottom of page