top of page
  • Writer's pictureየመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ

"ልጋብዝህ እንጂ አብረን እንስራ ማለት ባዕድ ሲሆንብን. " (ቡርሐን አዲስ)


እንደ አንድ ግለሰብ በአካባቢየ በተለያ የአጋጣሚ ብዙ ህብረት አለኝ። ብዙ ሰውጋ ትውውቅ አለኝ። የልብ ወዳጅ ማፍራት አለመቻሌ ያልፈታሁት ጥያቄ አለ። ወዳጅነት ምንድነው ስለሚለው ጥያቄ የሚያረካ መልስ አላገፕኘሁም። ምናልባት እኔ ራሴ ጥሩ ወዳጅ ለመሆን ብቁ አለመሆኔን ወስጃለሁ። የራሴ በሆነ ጉዳይ ኃላፊነት ስለምወስድ በራሴ ላይ ብይን ሰጥቻለሁ።


"ኢትዮጵያኖች አብረው ይበላሉ እንጂ አብሮ መስራት አይወዱም" ይላል አንድ የታወቀ የአውሮፓ ፀኃፊ። ትዝብቱ ልክ ይሆን አላውቅም። ፍርዱን ለየገጠመኛችን ልተው።


በራሴ ክበብ ውስጥ በታዘብኩት ግን ትዝብቱን 'እምም' እያለኝ ተቀብየዋለሁ። እስካሁን ባሳለፍኳቸው የኑሮ ሽቅብ ትግሎች ከብዙዎች ጋር የኪዳን ውል አድርጌ ጉዙዎች ጀምሬያለሁ...። ከልብ በሆነ አመኔታም መተማመን ስለነበረኝ ብዙ እኔየን አዋጥቻለሁ። ግን እንደምጠብቀው ጥሩ ፍጻሜ አላገኘሁም። ችግሩ ምንድንነው? ብየ ምብዙ አስቤያለሁ። ነገሩን ብዙሰው እንደሚጋራውም አስተውያለሁ። እናም እንደተባለው አብሮ መስራትና በጋራ መላቅን አንመርጠው ይሆን?


አብረን በአንድ ማዕድ እየበላን... በስራ መተሳሰብን ለምንገፋን? ጥሩ የህልም ቃል ገብተን እያለ በተግባር ግን ዝንጋታችን ምን ይሆን? ሁላችሁም በየራሳችሁ የምትሉት ይኖራል። በኔ የዛሬ ስሜት ግን በሰዎች ላይ ያለኝ ጠንካራ እምነት የጠወለገ ይመስለኛል።


እርግጥ ነው ችግሩ የኔው ነው... የልብ ህብረት ከማይኖረኝ የሰው ኃይቅ መገናኘቴ ይመስለኛል። ሁሉም ሰው የልቡ የሆነ አጋር ይኖረዋል። እንንከን ከገጠመው እውነታው ምርጫው ስህተትነው ማለትነው። በኔም ላይ ስፈርድ የሰፈር ምርጫየን ስህተትነት አስምሬያለሁ።


ከሰዎች ጋር ህብረት ከመፀነስህ በፊት የልብ ህብረት የምትፈጥርባቸውን ፈልግ። ከሀሳብ ይልቅ የልብ ቋንቋ ብዙ ያግባባል።


ቡርሐን አዲስ

64 views0 comments
bottom of page