top of page
  • Writer's pictureየመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ

“ብልጽግናና የጉራጌ ዞን አመራር” ከታዘብኩት (ታዬ ተስፋዬ ስሜ)


“ብልጽግናና የጉራጌ ዞን አመራር” ከታዘብኩት (ታዬ ተስፋዬ ስሜ)

“ብልጽግናና የጉራጌ ዞን አመራር” ከታዘብኩት (በአቶ ታዬ ተስፋዬ ስሜ)


በግሌ የመደምር አስተሳሰብና የብልጽግና መንገድና መዳረሻ በመድረኮች ስልጠናና እና ከመጻህፍት ንባብ በጥቂቱም ቢሆን ግንዛቤ ለማግኘት ሞክሬያለሁ በጣም በርካታ ሀሳቦች ዉስጤን ይማርኩኛል በተለየም የፖሊተካል ኢኮኖሚ ስብራቶች ና መፍትሄዎች በሙሉ እይታ የተተነተኑ በመሆናቸዉ ከድህነት መዉጫ በርም ይሆናሉ ብዬ አምናለሁ:: ግን ደግሞ በመጻሀፍት የተጻፉና አማላይ ሃሳቦች ወደ ተጨባጭ ፖሊሲና ፕሮግራም ተለዉጠዉ ማህበረሰቡን ከመጥቀም አንጻር ደምቀዉ አልታዩምና ስጋቴ ሃሳብና ተግባር ለየቅል ሊሆኑ እንደሚችሉ ከአብዮታዊ ዲሞክራሲ አዘጋጆች ተምሬያለሁ እንደ ቀድሞዉ ትንሽም ቢሆን ሳያዩ የሚያምኑ ካድሬ መሆን ደግሞ አልፈልግም:: ምክንያቱም ለዉጡ ከመጣ 3 ዓመት ወዲህ የመደመር እሳቤ በማስተዋወቅና በሱ የተቃኙ ፖሊሲዎችና ፕሮግራሞች ማስተዋወቅና ተግባር ላይ ማዋል ከኦሮምያ አማራና እና ሶማሌ ክልል ለህዝቡ የሚደረጉ የልማትና የስራ አድል ፈጠራ አይተን የደቡብ ክልል ለዉጡን አስፈጻሚ አመራሮች ከአብዮታዊ ዲሞክራሲ ከተባለዉ መስመር ያልወጡና በዛዉ እሳቤ ደረጃ ላይ ያሉና ተቸካይ ሆነዉ የቆሙ በመሆናቸዉ ነዉ::

ይቺን ያህል ከለዉጡ አንጻር ካልኩኝ የጉራጌ ዞን ብልጽግናን በዞን ደረጃ እንዲመሩ የተረመጡ አካላት ስመለከት ቀድሞ አብዮታዊ ዲሞክራሲ ከተባለዉ አስተሳሰብ እንኳ ዲሞክራሲን አጥፍተዉ በአብዮት ብቻ የሚመሩ ጨቋኝና የአለቃ እና ምንዝር አስፈጻሚዎች የነበሩ ናቸዉ እነዚህ አካላት የበታቾቻቸዉን በመጨቆን አለቆቻቸዉን ከፈጣሪ በታች ጌታ አድርገዉ እግራቸዉን ዘርግተዉ ጭራቸዉን የሚቆሉ አስመሳዮች ናቸዉ መገለጫቸዉም ከማንበብ ከማወቅና ከመጠየቅ ይልቅ በየመድረኩ አለቆቻቸዉ የሚናገሩትን ቅንጥብጣቢ ሃሳቦች በአጀንዳቸዉ ሸክፈዉ በመምጣት በአገኙት መድረክ ሁሉ አሰልቺና ከእዉቀት ነጻ የሆኑ ዲስኩሮችን ሲተረትሩ ስታይ ትሸማቀቃለህ ቁጥሩ ቀላል ያልሆነ ተከታይ አመራርም አሰላለፉ የራሱና የቤተሰቡን ንሮን ለማሸነፍ እንጂ/household asset building/ የህዝብን የልማትና የዲሞክራሲ ጥያቄ ለማስፈጸም የተዘጋጀ እንዳልሆነ ለመረዳት ከየቢሮዉና ከየስብሰባዉ የሚያገኘዉን አበል እያሰላ መድረክ የሚያዳምጥ በመሆኑ መድረክ መሪዉ የሚለዉ ሃሳብ ብዙም ግድ አይሰጠዉም ግድ ከሰጠዉም አንገቱን አቀርቅሮ ከማጉረምረም ዉጪ ሌላ መላ የሌለዉ ነዉ። የተወሰኑት ደግሞ እንደ አጠቃላይ አዋቂ/generalist/ በተከፈቱ መድረኮች ሁሉ እጃቸዉን በማንሳት አለቆቻቸዉ የሚያስደስት ቡራኬ እና ሌላዉን የሚወቅስ ሃሳቦችን በመስጠት የሚታወቁ ናቸዉ ከመድረክ ከቀረበዉ የተለየ ሃሳብና እይታ ያለዉ ሰዉ ከተገኘማ እሱን በመርገም ጀግነዉ የአመራርነት አድሜያቸዉን ታጋይ በሚል ማዕረግ ያስረዝማሉ፡፡ እዚህ ላይ ሁሉም መጨፍለቅ እንዳሆንብኝ በእዉቀትና በትጋት ስራቸዉን የሚሰሩ ጠንካሮችም እንዳሉ ይያዝልኝ፡፡

ጥቂቶቹግን እኔን ጨምሮ አብዛኛዉ ሰዉ ወጣት መሳይነታቸዉን እና በዞን በከተማና በወረዳ መድረክ ለህዝብ እንደቆሙ የሚመስሉ እንዲሁም በሶሻል ሚድያ በፌክ አካዉንት ጭምር ፕሮፖጋንዳ ሚነዙ በተግባር ግን የሴራ ፖለቲካ አራማጆች ሆነዉ በእኩልነትና በፍታሃዊነት የማያምኑ ኅላ ቀሮች ሲሆኑ ከላይ እንደጠቀስኩትም ወደ ክልል ሲሄዱ አፋቸዉ ሚዘጋና እንኳን ትላልቅ የህዝብ ጥያቄዎች ታግለዉ የሚጠይቁና የሚያመጡ ቀርቶ የተሰጣቸዉን ይዘዉ ለመምጣት የሚሽኮረመሙ ናቸዉ።

በወረዳ ደረጃ ያሉትን አብዛኛዉ አዲስ ሃይል በመሆናቸዉ የተግባር ዝግጁነታቸዉ የሚያስመሰግን ነዉ በእዉነትና በእዉቀትም የሚታገሉ በርካቶች አሉ ኋላ ቀርና ሴረኞቹ ካላጠፉዋቸዉ በስተቀር። በተመሳሳይ መልኩ በተወሰኑ ወረዳዎች ያሉትን ስትመለከት ስርዓቱን ሞናሪኪያል በማስመሰል ቤተሰቦቻቸዉን ወዳጆቻቸዉን በመሰብሰብ ህዝብን የሚያማርሩ እንኳን ልማት ሊሰሩ የተሰራዉንም የማይጠብቁ ጊዜያቸዉን በወሬ እና አሉባልታ የሚሳልፉ ለዞን አለቆቻቸዉ መረጃ በማቀበልና አለቆቻቸዉ ያዘዛቸዉን እንጂ ህዝቡ ሚፈልገዉን የማይሰሙ አመጣጣቸዉም በድሮ ትዉዉቅና በዉለታ መላሽ አይነት የተሰገሰጉ ናቸዉ እናም በራሳቸዉ ዉሳኔ የማይወስኑ የስልጣን ቆይታቸዉም በዞን አመራር እጅ እንደሆነ የሚያስቡ እንኳን ህዝብ እራሳቸዉን የማያሻግሩ ከምርጫ ማግሰት በህዝብ ትግል ቅርብ ወራጅ አመራሮች ናቸዉ፡፡ ይህንን ሀሳብ የፃፍኩት አብዛኛው ሰው አሁን ያሉት አመራሮች የጉራጌን ጥያቄን ታግለው ያስፈጽማሉ ብሎ እንዳይዘናጋ በማሰብ ነው።

በቀጣይ ሌላ ትርጉም ካልተሰጠዉ በስተቀር ባለፉት ጊዜያት በነበሩና አሁንም ባሉ የጉራጌ ሴረኛና ከፋፋይ ከፍተኛ አመራሮች ምክንያት ጉራጌ ዞን በራሱ አስተዳደር ዉስጥ የኢኮኖሚና ፖለቲካል እኩልነት እንዳይኖር በማድረግ የህዝቡን አንድነት የሚፈታተኑ ተግባራት ላይ የታዘብኳቸዉን አቀርባለሁ።

አመሰግናለሁ!

ታዬ ተስፋዬ ስሜ

48 views0 comments
bottom of page