top of page
  • Writer's pictureየመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ

ዜና መስቃን በጎ አድራጎት ድርጅት

Updated: Jul 30, 2020


መስቃን በጎ አድራጎት ድርጅት
መስቃን በጎ አድራጎት ድርጅት

እሁድ ሐምሌ 19 2012 (July 26 2020) የመስቃን በጎ አድራጎት ድርጅት አለም አቀፍ ስብሰባ (online Zoom meeting) አካሄደ በስብሰባው በተለያዩ አለም አቀፍ ሀገሮች ውስጥ የሚገኙ የቤተ መስቃን ተወላጆች እና የበጎ አድራጎት ድርጅቱ የስራ ሃላፊዎች የተሳተፉ ሲሆን የድርጅቱ ምስረታና ዋነኛ አላማ ማህበረሰቡን መሰረታዊ የሆኑ የልማት ፍላጎቶችን ለማሟላት በህዝብ የተቋቋመ ድርጅት እንደሆነ የቦርድ ሊቀመንበር አምባሳደር ድንበሩ አለሙ ተናግረዋል።


ክቡር አምባሳደሩ አክለው እንደተናገሩት ድርጅቱ ለመስቃን ህዝብ ከልማታዊ እንቅስቃሴው በተጨማሪ በዘረፈ ብዙ ጉዳዮች አይንና ጆሮ ሆኖ ጭምር እንደሚሰራ አሳውቀዋል። በስብሰባው በርካታ የሆኑ ጉዳዮች የተዳሰሱ ሲሆን የበጎ አድረጎት ድርጅቱ የማህበረሰቡን ችግር ከመቅረፍ አንጻር ረጅም ርቀት እየተጓዘ እንደሆነ የቦርድ ሊቀመንበር እና በተለያየ የስራ ዘርፍ የሚሰሩ የድርጅቱ የስራ አመራር አካላት አሳስበዋል። በተጨማሪም ስብሰባው የተካፈሉ በአሜሪካ፣ እንገሊዝ እና ሳዑዲ አራቢያ ነዋሪ የሆኑ የቤተ መስቃን ተወላጆች የበጎ አድራጎት ውጥን ስራዎች ይሰምሩ ዘንድ አስፈላጊው እገዛ ሁሉ እንደሚያደርጉ ቃል ገብተዋል።

የመስቃን በጎ አድራጎት ድርጅት በአዲስ አበባ የዋናው መስሪያ ቤት ቢሮ የሚገኝ ሲሆን በቡታጅራ እና በሳውዲ አረቢያ ሪያድ ከተማ ቅርንጫፍ ቢሮዎች እናዱሉት የቦርዱ ሰብሳቢ አሳውቀዋል። በቀጣይ በተለያዩ የማህበረሰቡ ተወላጆች በሚገኙበት የኢትዮጵያ ክልሎች፣ በሰሜን አሜሪካ ፣ አውሮፓና ደቡብ አፍሪካ ቅርንጫፎች እንደሚከፍት ጭምር አሳውቀዋል።


በዚህ አለም አቀፋዊ የኦንላይን ስብሰባው የቡታጅራ ቅርንጫፍ የስራ አመራር አካላት፣ የሪያድ ቅርንጫፍ የስራ አመራር አካላት በአሜሪካ ነዋሪ የሆኑ የቤተ መስቃን ተወላጆች ፣ በእንግሊዝ ሃገር ነዋሪ የሆኑ የቤተ መስቃን ተወላጆች እና የመስቃን ሚድያ ኔትዎርክ ተወካዮች ተሳታፊዎች ነበሩ።

122 views0 comments
bottom of page