top of page
  • Writer's pictureየመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ

የመስቃን ልማት ማህበር ቡታጅራ ቅርንጫፍ


ቅዳሜ ኦክቶበር 12 2019 የመስቃን ልማት ማህበር ቡታጅራ ቅርንጫፍ ከባለድርሻ አካላትና ከውስን አባላት ጋር በመሆን ወሳኝ ስብሰባ አካሄደ:: በመንግስት ተደራሽ ያለሆኑ የመስቃን ማህበረሰብ ችግሮችን በአለም ዙሪያ የሚኖሩትን የመስቃን ተወላጆችን በማካተት የማህበረሰቡን ችግር ለመቅረፍ እንዲሁም በሰላምና በልማቱ ዘርፍ መንግስትን ለማገዝ ጥረት መደረግ እንዳለበት ለውይይት ቀርቧል። ለዚሁም ሁሉም ቤተ መስቃን ተወላጆችን በአካባቢው የሚኖሩ የልማት ማህበሩ አባል ለማድረግ እንቅስቃሴዎችን መጀመር እንዳለበት ያሳወቁ ሲሆን የቤተ መስቃን ተወላጅ አባል ሆኖ መመዝገብ ከክፍፍል እና በታኝ አመለካከት ወጥቶ በልማትና ሰላሙ ዘርፍ ቤተ መስቃንን እና መንግስት ለመደግፍ መነሳቱን ማረጋገጫ እንደሚሆን ጭምር አሳውቀዋል።

ከስብሰባው ተሳታፊዎች ይህ መዋቅር ስር ነቀል ለውጥ እንዲያመጣ መጠናከሩ አማራጭ የሌለው መንገድ እንደሆነ አሳስበዋል ። የልማት ስራውን ለማጠናከር አመራር በሚንቀሳቀስበት ወቅት የልማት ማህበሩን መጠናከር የማይፈልጉ አካላት ለማደናቀፍ ሙከራ ቢያደረጉ እንኳን በትዕግስትና በትጋት መስራት እንዳለበት እና ወደ ዃላ የማያፈገፍጉበት ጉዳይ መሆኑን ከተሳታፊዎች በአጽኖት ተገልፆአል። በተጨማሪም ለቤተ መስቃን፣ ለአጎራባች አካባቢዎች እና ለኢትዮጵያውያን በመሉ ሰላም፣ ዕድገት እና ብልጽግና ሁሉም በአንድነትና በተባበረ ክንድ ሰፊ ስራ መስራት እንዳለበት በስፋት ተዳስሷል።

የልማት ማህበሩ መልሶ የማቋቋሙን ሂደትና አላማ የተወሰነው የማህበረሰብ ክፍል የመረጃ አጥረት ስላለበት በቅጡ አለመረዳቱ ያሳያል በማለት የመስክ ስራ የወጡ የንዑስ ኮሚቴ አመራር አካላት አሳስበዋል። ለዚሁም የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራው በሁሉም አቅጣጫ በሰፊው በሁሉም የልማት ማህበር አማራር ኣካላትና አባላት መሰጠት እንዳለበት አቅጣጫ ተቀምጣል።

በቡታጅራ የሴቶች ልማት ማህበር ሊቀመንበር ወ/ሮ ሄርያ መሃመድ የስብሰባው ተሳታፊ የነበሩ ሲሆን የመስቃን ልማት ማህበር በህጋዊ መንገድ መቋቋም የዳግም ውልደት ያህል መነሳሳትን ጥንካሬን የፈጠረባቸው መሆኑን በስሜት የገለጹ ሲሆን በልማትና ሰላም እንቅስቃሴው የሴቶች ተሳትፎ ለማበራከት በሰፊው እንደሚሰሩ አሳውቀዋል።

በእለቱ ስብሰባውን ይመሩ የነበሩት የቦርድ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ሃይሩ ስርጋጋ የልማትና የሰላምን ሂደት በተሻለ መልኩ ለማስቀጠል በሃገር ውስጥ እና ካሀገር ውጪ የሚኖሩ ሁሉም የቤተ መስቃን ተወላጆች የሚሳተፉበት እቅድና መዋቅር እንደተዘረጋ ያሳወቁ ሲሆን ይህንኑ ለማሳካት አዲሰ አበባ የሚገኘው የእናት ልማት ማህበር፣ የቡታጅራ ቅርንጫፍ እና በሪያድ ሳዑዲ አረቢያ የመስቃን ልማት ማህበር ቅርንጫፍ ተጣምረው እየሰሩ መሆናቸውን አሳውቀዋል። አቶ ፋንታዬ አለማየሁ የመስቃን ልማት ማህበር የቦርድ ጸሃፊ በተመሳሳይ የቦርድ ምክትል ሰብሳቢው የገለጹትን ከስኬት ለማድረስ የማይፈነቀል የጥረት ድንጋይ እንደማይኖር በአጽንዎት ተናግረዋል። አቶ ሰመሩ ስርዋጃ በሁለቱ የመስቃን ወረዳዎች የመስቃን ልማት ማህበር አስተባባሪ ኮሚቴ ሰብሳቢ ሲሆኑ የልማት እና የሰላም የስራው ሂደት ይሳካ ዘንድ ከሁሉም ቅርንጫፍ የመልማ አመራሮችና ጋር በመሆን መላው ቤተ መስቃን ለማሳተፍ የበኩላቸውን ጥረት እንደሚያደርጉ አሳውቀዋል።


አወል አህመዲን

ለመስቃን ሚድያ ኔትዎርክ ከቡታጅራ

110 views0 comments
bottom of page