top of page
  • Writer's pictureየመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ

ሪህ ምንድነዉ? እንዴትስ ሊመጣ ይችላል? መከላከልስ ይቻላል? / Goutሪህ በመገጣጠሚ ላይ በተለይ ደግሞ በእግር ትልቁ ጣት ላይ በድንገት የሚጀምር ከፍተኛ ህመም ስሜት፣እብጠትና መቅላት የሚመጣ የህመም አይነት ነዉ፡፡ሪህ ከሴቶች ይልቅ ወንዶች ላይ በብዛት የሚከሰት ቢሆንም ሴቶች ካረጡ በኃላ ለህመሙ ተጋላጭነታቸዉ እየጨመረ ይመጣል፡፡

የህመሙ ምልክቶች የሪህ የህመም ምልክቶች ብዙዉን ጊዜ ያለማስጠንቀቂያ በድንገት የሚከሰት ሲሆን በብዛት የሚጀምረዉ ማታ ላይ ነዉ፡፡ የህመሙ ምልክቶች • ከፍተኛ የሆነ የመገጣጠሚ ላይ ህመም፡- ምንም እንኳ ሪህ በአብዛኛዉ የሚከሰተዉ የእግር አዉራ ጣት ላይ ቢሆንም በእግር መዳፍዎ፣በቁርጭምጭሚትዎ፣ በጉልበትዎ፣ በእጅዎ መገጣጠሚያዎች ላይ ሊከሰት ይችላል፡፡ ህመሙ ከጀመረ የመጀመሪያዎቹ ከ4 እስከ 12 ሰዓታት ዉስጥ በጣም ሊባባስ ይችላል፡፡ • ቀጣይነት ያለዉ የህመም/ምቾት ያለመሰማት ስሜት፡- ከፍ ያለዉ ህመም ካለፈ በኃላ የተወሰነ ህመምና ምቾት ያለመሰማት ከቀናት እስከ ሳምንታት ድረስ ሊቀጥል ይችላል፡፡ • የመቆጥቆጥና የመቅላት ስሜት፡- በህመሙ የተጎዳዉ መገጣጠሚያ የማበጥ፣ ሲነካ የማመምና መሞቅ ስሜት እንዲሁም የመቅላት ባህሪ ይኖረዋል፡፡ • እንቅስቃሴ መገደብ፡- ህመሙ እየፀና ሲመጣ መገጣጠሚያዉ መታዘዝ/መንቀሳቀሱን ይቀንሳል፡፡ ከላይ የተጠቀሱት የህመም ምልክቶች ካሎት ህክምና ማግኘት ያስፈልጋል፡፡ ህመሙ ከመጣ በኃላ ህክምና ሳይደረግ በራሱ ጊዜ ከጠፋ ህመሙ እየተባባሰና መገጣጠሚያዉን ስለሚጎዳዉ መታከም ያስፈልጋል፡፡

የህመሙ ምክንያት ሪህ የሚከሰተዉ ዩሬት ክሪስታል የሚባለዉ ኬሚካል መገጣጠሚያ ዉስጥ ተጠራቅሞ የመቆጥቆጥ ስሜት/ inflammation/ እንዲጀምር ወይም እንዲነሳ በማድረግ የህመሙ ምልክቶች እንዲመጣ ያደርጋል፡፡ዩሬት ክሪስታል የሚመጣዉ በደማችን ዉስጥ የዩሪክ አሲድ መጠን ከሚፈለገዉ መጠን በላይ ከፍ ሲል ነዉ፡፡ ሰዉነታችን ዩሪክ አሲድን ፕዩሪንስ የሚባሉ ኬሚካሎችን በሚሰባብርበት ወቅት የሚመረት ሲሆን ፕዩሪንስ በተፈጥሮ በሰዉነታችን ዉስጥና በተወሰኑ እንደ ስጋና የባህር ምግች ዉስጥ ይገኛል፡፡ በተጨማሪም ከፍ ያለ ዬሪክ አሲድ በሰዉነታችን እንዲኖር ከሚያደርጉ ነገሮች ዉስጥ አልኮሆል(በተለይ ቢራ) እና እንደ ፍሩክቶስ ባሉ የፍራፍሬ ስኳር የጣፈጡ መጠጦች መጠጣት ናቸዉ፡፡ ዩሪክ አሲድ በደምዎ ዉስጥ በመሟሟት ከሰዉነትዎ በኩላሊት አማካይነት እንዲወገድ ይደረጋል፡፡ ነገርግን ሰዉነታችን ከሚፈለገዉ መጠን በላይ ዩሪክ አሲድን ካመረተ አሊያም ኩላሊትዎ ከሚገባዉ በታች ከሰዉነታችን እያስወገደች ከሆነ የዩሪክ አሲድ መጠን በሰዉነታችን ዉስጥ በመጨመር ዩሬት ክሪስታል በመገጣጠሚያ ዉስጥ እንዲፈጠር በማድረግ የህመም ስሜቶች እንዲከሰት ያደርጋል፡፡ ተጋላጭነተወዎን የሚጨምሩ ነገሮች በሰዉነትዎ ዉስጥ በጣም ብዙ ዩሪክ አሲድ ካለዎ ሪህ ሊከሰት ይችላል፡፡

በሰዉነትዎ ዉስጥ የዩሪክ አሲድ መጠን እንዲጨምር ከሚያደርጉ ምክንቶች ዉስጥ • አመጋገብ፡- አመጋገብዎ ዉስጥ ስጋ፣ የባህር ምግችን/seafood/፣ በፍሩክቶስ የፍራፍሬ ስኳር የጣፈጡ መጠጦች፤ አልኮሆል(በተለይ ቢራ) ማዘዉተር የዩሪክ አሲድ መጠን እንዲጨምር ስለሚያደርጉ ለሪህ ህመም ተጋላጭነትዎን ሊጨምር ይችላል፡፡ • ዉፍረት፡- ክብደትዎ ከመጠን በላ ከሆነ ሰዉነትዎ ብዙ ዩሪክ አሲድ እንዲያመርት ስለሚያደርግና ኩላሊትዎ ላይ ጫና ስለሚፈጥር ለሪህ ያጋልጥዎታል፡፡ • የዉስጥ ደዌ ችግሮች፡- የስኳር ህመም፣ የልብ ችግር፣ ያልታከመ የደም ብዛት፣ ሜታቦሊክ ሲንድረምና የኩላሊት ችግር ካለዎ ለሪህ ተጋላጭነትዎ ይጨምራል፡፡ • መድሃኒት፡- ለደም ብዛት ህክምና ሊሰጥ የሚችሉ እንደ ታያዛይድ ዳይዩሬቲክስና ሌሎች እንደ አስፒሪን ያሉ መድሃኒቶች የዩሪክ አሲድ መጠንን ሊጨምሩ ይችላሉ፡፡ • በቤተሰብዎ ዉስጥ መሰል የጤና ችግር ካለ፡- አንዱ የቤተሰብዎ አባል መሰል ችግር ከነበረዉ እርስዎም በችግሩ የመያዝ/የመጠቃት እድልዎ ከፍተኛ ነዉ፡፡ • እድሜና ፆታ፡- ከሴቶች ይልቅ ወንዶች በወጣትነት እድሜያቸዉ ሪህ ሊይዛቸዉ ይችላል፡፡ ሴቶች እድሜቸዉ እየጨመረ ሲመጣና በተለይ ሲያርጡ ለሪህ ተጋላጭነታቸዉ እየጨመረ ይመጣል፡፡ • ከአደጋ በኃላ ቀዶ ጥገና በቅርቡ ተደርጎሎት ከነበረ ለሪህ ሊደረጉ የሚችሉ ምርመራዎች • ፈሳሽ ካለ ናሙና ተወስዶ መመርመር • የደም መርመራ • ራጅ • አልትራሳዉንድ የማሳሰሉት ናቸዉ፡፡

የኑሮ ዘይቤና የቤት ዉስጥ ህክምና ምንም እንኳ ዋናዉ ህክምና መድሃኒት መጀመር ቢሆንም የተወሰኑ የኑሮ ዘይቤ ለዉጥ ማድረግ ህመሙን ለመቀነስ ሊረዳዎ ይችላል፡፡ • የሚወስዱትን የአልኮል መጠጥና በፍራፍሬ ስኳር/ፍሩክቶስ/ የጣፈጡ መጠጦችን መገደብ፡- ከነዚህ ይልቅ ዉሃ በብዛት በጠጣት • የፕዩሪን መጠናቸዉ ከፍተኛ የሆኑ እንደ ቀይ ስጋ፣የባህር ምግቦችን ያለማዘዉተር • መደበኛ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግና ክብደትን መቀነስ ሪህን እንዴት መከላከል ይቻላል?

የህመም ምልክቶች በሌሉበት ወቅት ተጨማሪ የህመም ስሜቶች እንዳይመጡ • ፈሳሽ በብዛት መዉሰድ፡- ዉሃ በደንብ መጠጣት • የአልኮል አወሳሰድዎን መገደብ፡- • የፕሮቲን ምንጭዎን መጠነኛ ስብ ከሚሰጡ የእንስሳት ተዋፅኦ ዉጤቶች ማድረግ • የስጋ፣የዓሳና የዶሮ ምግችን መመጠን • ክብደት መቀነስ ናቸዉ፡፡

ምንጭ - ጤና ማህደር


328 views0 comments
bottom of page