• የመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ

"አስተውሎት እና ትኩረት"አቀበት ተጠይቆ ሲመልስ "ወጣቱን ረታሁት። ሽማግሌው ግን ረታኝ" አለ።

ያ... ወጣት ባለ አቅም እና ባለ ወኔ ነኝ ብሎ እራሱን ስለሚፈርጅ አቀበቱን በሩጫ ይያያዘውና ብዙም ሳይርቅ አለክልኮ ይወድቃል።

ሽማግሌው ግን ወጉ እያወጋ ፣ ዝግ ብሎ እና እያረፈ ይጓዛል። ካሰበበትም ያለ ብዙ ድካም እና እንግልት ይደርሳል። ለዚሁም ነው ለአቀበት እጅ ያልሰጠው ወይም ያለተንበረከከው።

አንዳንዴ ወይም ሁል ጊዜ ማስተዋል ያልታከለበት እንቅስቃሴ ከስኬት ማማ ላይ አያፈናጥጠንም። አስተውለውና በእቅድ እየተመሩ የሚደረግ እንቅስቃሴ ስኬትን ከመቆናጠጥ ሊገታው የሚችለው ተፈጥሯዊ ሃይል ብቻ ነው።

ሩሲያውያን "አስር ጊዜ ለካ ነገር ግን አንዴ ብቻ ቁረጥ" ይላሉ።

እናስተውል ጎበዝ ! "የፈሰሰ ውሃ አይታፈስምና"።


13 views0 comments

Copyright © 2018 Meskan Media Network - All Rights Reserved. E-mail : meskanmedia@gmail.com

  • YouTube - White Circle
  • White Spotify Icon
  • White Apple Music Icon
  • White Amazon Icon
  • White Facebook Icon
  • Twitter Clean