top of page
  • Writer's pictureየመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ

ለአፍንጫ መድማት / ነስር ሊደረግ የሚችል የመጀመሪያ ደረጃ ህክምና



ነስር በጣም የተለመደ የአፍንጫ መድማት ችግር ነዉ፡፡ ይህ ክስተት ብዙዉን ጊዜ የሚመጣዉ በመሰረታዊ የጤና ችግር ምክንያት ያልሆነና ሊረብሽዎ/ሊያናድድዎ የሚችል ችግር ነዉ፡፡

ሊደረግ የሚችል እንክብካቤ • ቀጥ ብሎ ወደ ፊት ትንሽ ዘንበል ብሎ መቀመጥ፡- ቀጥ ብሎ መቀመጥ የአፍንጫዎን የደም ግፊት መጠን ለመቀነስ ያግዝዎታል፡፡ ወደፊት ማዘንበልዎ ደግሞ ደሙን እንዳይዉጡት ለመከላከል ይረዳዎታል፡፡ • አፍንጫዎን ጫን አድርገዉ/ቆንጥጠዉ መያዝ፡- አፍንጫዎን በአዉራ ጣትዎና በጠቋሚ ጣትዎ ከ5 እስከ 10 ደቂቃዎች በደንብ በመያዝ የአፍንጫ ቀዳዳዉን አፍኖ መቆየትና በአፍዎ መተንፈስ፡፡ አፍንጫዎን በደንብ አድርገዉ መያዝ በሚደማዉ የደም ቧንቧ ላይ ግፊት ስለሚፈጥር መድማቱን እንዲያቆም ያደርጋል፡፡ • በድጋሚ እንዳይደማ መከላከል፡- የአፍንጫዎ መድማት ካቆመ በኃላ ለተወሰኑ ሰዓታት አፍንጫዎን ያለመጎርጎር ፣ ያለመናፈጥና ወደታች ያለማጎንበስ፡፡ በዚህን ጊዜ በተቻለ መጠን የራስ ቅልዎን/አፍንጫዎን ከልብዎ በታች ያለማድረግ፡፡ • እንደገና መድማት ካጋጠመዎ፡- እንደገና መድማት ካጋጠመዎ የረጋዉን ደም ለማሶጣት መናፈጥ፤ ከዚያን ኦክሲሜታዞሊን ናዛል ዲኮንጀስታንት ስፕሬይ በአፍንጫዎ በሁለቱም በኩል መርጨት፡፡ አፍንጫዎን እንደገና ከላይ በተጠቀሰዉ መንገድ መያዝና የህክምና ባለሙያዎን ማማከር፡፡

ድንገተኛ ህክምና ማግኘት የሚገባዎ መቼ ነዉ? • መድማቱ ከ20 ደቂቃዎች በኃላ ከቀጠለ • የአፍንጫ መድማቱ አደጋን ተከትሎ የመጣ ከሆነ (የመዉደቅ፣መመታት)

የህክምና ባለሙያዎን ማማከር የሚገባዎ መቼ ነዉ? • በተደጋጋሚ መንሰር ካጋጠመዎ • የደም ማቅጠኛ መድሃኒቶች እየወሰዱ ነስር ካጋጠመዎ፡- እንደ ዋርፋሪንና አስፒሪን የመሳሰሉ መድሃኒቶችን እየወሰዱ ከሆነና የአፍንጫ መድማት ካጋጠመዎ መድሃኒቱን ማስተካከል ሊያስፈልግ ስለሚችል የህክምና ባለሙያዎን ማማከር፡፡


93 views0 comments
bottom of page