top of page
  • Writer's pictureየመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ

የ27 አመታት ትሩፋቶች ልክፍት



 ከ27 አመታት ትሩፋቶች መካከል ሁሉም የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ክፍል ያለ ገደብ የተቋደሰው ቢኖር ዘረኝነትን እና አለመግባባትን ነው። ታዲያ እኛም ከእዚያ ውስጥ ተዱለን ብንገኝ እንኳን እነ ዘረ አዳም/ሔዋን ቅር ሊሰኙ  አይገባቸውም። ለምን ቢሉ ? ሁሉም የኢትዮጵያ የማህበረሰብ ክፍል ፣ ከሊቅ እስከ ደቂቅ ወይም ፊደል ያልቆጠረው የማህበረሰብ ክፍልና በእውቀቱ የሰማይን ጥግ የነካው ምሁር ጭምር ልኬቱ ቢለያይ እንጂ  ዘረኞች ናቸው። እንድየውም ዘረኝነትን እያጦዘው እና ማህበረሰብን ከማህበረሰብ እያጋጨ የሚገኘው ተምሬአለሁ… አውቄአለሁ የሚለው የማህበረሰብ ክፍል እንደሆነ ሃገሩ ሁሉ የሚያውቀው ጉዳይ ነው።

 ዘመኑ የነቀፌታ ዘመን ነውና ምናልባት… ምናልባት  አንተ ማን ነህና ? እንዳሻህ የምትዘረጥጠው ወይም የምትዘረጠጠው የሚል ይከሰት ይሆናል። አዎን… እኔ በተዋከቡ፣ በእናውቅልሃለን አዕምሮአቸው የጦዘ እና  በክፋት የሰኩሩ መሪዎች በፈጠሩት የተዋከበ ማህበረሰብ ውስጥ የተከሰትኩ ነኝ። ታዲያ እኔም ተዋክቤ አፌን ብከፍት አፍህን ከፈትክ አትበሉኝ ! ሃይማኖተኛው፣ ምሁሩ፣ ቀማኛው፣ መጋኛው፣ ፖለቲከኛው ፣ ወንድ፣ ሴት፣ ወጣት፣ጎልማሳ፣ ሽማግሌ እንዲሁም አዛውንት “ከፍተው”… ያልነበሩ ከተገኙ የእኔው የዛሬው መክፈት ማስተካከያ ሊደረግለት የሚያስችል እድል ይኖራል።           

 ዘመኑ የወሬ ዘመን ነውና ወሬ ለመቃረም ወደ FB መንደር ዘልቄ ነበር። “ ስለ እሳት መቆሰቆና ሲቆሰቆስ መንደዱን ይጨምራል " የሚል ከተራ ጽሁፎች መሃል ሰፍሮ በማየቴ የ27 አመት ትሩፋት ውጤት ስለሆነ፣ እኔን እና እኛን የሚመለከት ስለነበር አንድ ለማለት ወደድኩ።

 ከጽሁፉ እንደምረዳው እሳትን ጠቅሶ ስለ እሳት መቆስቆስ ከተነሳ የተዳፈኑ ጉዳዮች እንዳሉ አመላካች ነው። ታዲያ የተዳፈኑት ጉዳዮች ላይ ማስተካከያ ሳይደረጉ እንዲሁም የተዳፈነውን እሳት ሳይጠፉ ወደ የት ለመሄድ ይከጀላል?

ፍቅር፣ ሰላምን እና አንድነትን የሚጠላ ይኖራል ብዬ አላምንም ። ሰይጣንም ቢሆን እንኳን ሌሎችን ቢያሳሰትና የሌሎችን ሰላም ቢነሳ እንጂ የእራሱን ሰላም አይፈልግም ተብሎ አይገመትም።

ይቀጥላል


18 views0 comments
bottom of page