top of page
  • Writer's pictureየመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ

"ህይወት" ሰው እንደሚያስበው ይሆናል! ክፍል ሁለት"ህይወት" ሰው እንደሚያስበው ይሆናል! ክፍል ሁለት

ባደጉ ሃገሮች ዜጎችና በአብዛኛው ኢትዮጵያውያን መካከል ያለው ልዩነት አስተሳሰብ ብቻ ነው፡፡ በተረፈ ግን ከቀለማችን በስተቀር ፈጣሪያችን እኩል ፈጥሮናል፡፡ ለምሳሌ አንድ የተበተነ የመኪና ሞተርን ለመገጣጠም መጀመሪያ መካኒኩ ስለ ሞተሩ መለማመድ አለበት፡፡ ከዛም እያንዳንዱ የሞተሩን ክፍል በቅደም ተከተልና በቦታው ማስገባት አለበት፡፡ ሞተሩ ሲገጣጠም ስህተት ተሰርቶ መኪናው እንዳይቆም ወይም ትንሽ ፈቅ ብሎ እንዳይበላሽ መካኒኩ በስሜት ሳይሆን በምክንያት ሞተሩን መገጣጠም አለበት፡፡ ስሜት ለማዘን እንጂ ለስራ አይሰራም፡፡ መካኒኩ ድንገት ከተሳሳተና ሞተሩ እንዲሰራ ከፈለገ እንደገና ማስተካከል አለበት፡፡ ከስህተቱ ተምሮ፡፡ ሞተሩ ግን ባጋጣሚ አይገጣጠምም፡፡ ያ ከሆነ አይሰራም፡፡ ይህ ሞተር የሚገጠመው በተለማመደና በሚያውቅ መካኒክ ነው፡፡

አሁን መካኒኩን እንደ ኢትዮጵያዊ እንየው፡፡ የመኪናውን ሞተር ደግሞ እንደ ህይወት እንየው፡፡ ይህ ኢትዮጵያዊ ህይወት እንዴት እንደሚሰራ፣ እንዴት እንደሚገጣጠምና እንዴት እንደሚሄድ ማወቅ አለበት፡፡ ካላወቀ ወይም ካልተማረና ካልተለማመደ ግን ሞተሩ/ህይወቱ ይቆማል፡፡ ወይም ህይወቱ ይበላሻል፡፡ አሁን ኢትዮጵያዊው ህይወቱን በትክክል መገጣጠም ካልቻለ ሌሎች ስለ ህይወት የሚያውቁ የራሳቸውን ሞተር/ህይወት ገጣጥመው ያልፉታል፡፡ ኢትዮጵያዊው ግን እዛው ቆሟል፡፡ መጨረሻ ላይ ኢትዮጵያዊው ምግብ ማግኘት ወይም የሚፈልግበት ቦታ መድረስ ስላለበት አንገቱን ደፍቶ እርዳታ ይጠይቃል፡፡ ያዘነ ፍርፋሪ ይሰጠዋል፡፡ አንዳንዶቹ ይኸ የማይገባው ደግሞ ብለው ንቀውት ያልፉታል፡፡ ይህ ሁሉ የደረሰበት እያንዳንዱን የሞተር/የህይወት ክፍል በትክክል ስላልገጣጠመው ነው፡፡ በአስተሳሰቡ ትክክል ለመሆን ስላልተለማመደ ነው፡፡

ብዙ ኢትዮጵያውያን ትክክል መሆን አይፈልጉም፡፡ ትክክል ለመሆን በትንሽ ነገር እንኳን አልተለማመዱም፡፡ እኔ እራሴ ትልቅ ሰወች ናቸው ከምላቸው ሰወች ጋር ከሶስት አመት በፊት አካባቢ ጀርመን ሃገር ውስጥ ቢራ እየጠጣን ነበር፡፡ እና ሌላ ሰው ስልክ ደውሎ ለመምጣት የት እንዳለን ሲጠይቅ፤ ካጠገቤ ያለው በስልክ እዚህ ቦታ ላይ ሻይና ቡና እያልን ነው አለው፡፡ "ቢራ አደልም እንዴ የያዝነው? ለምን ሻይና ቡና አልከው?" ብዬ ስጠይቅ፤ "ምን አንተ ደግሞ ያው አደልም እንዴ?" ብለው ሳቁብኝ፡፡

በሌላ አጋጣሚ እዚሁ ኖርዌይ ውስጥ አንድ ከሌላ ሃገር የመጣ ወጣት ጋር በሆነ አጋጣሚ ማውራት ጀመርን፡፡ ምን እንደሚያደርግ ጠየኩት፡፡ ከፍተኛ የኤሌክትኖኒክስ ስራ እንደሚሰራ አይነት አድርጎ ነገረኝ፡፡ እኔም ስለጓጓሁና ደስ ብሎኝ የበለጠ ለማወቅ ምን አይነትና የትኛው ክፍል ብዬ ጠየኩት፡፡ በኋላ ግን ምንም ከነገረኝ ጋር ግንኙነት የሌለው ነገር መሆኑን አወኩ፡፡ ለእረፍት ወጥተው ሲመለሱ ብዙ አጋነውም የሚያወሩም አጋጥሞኛል፡፡ ገና ከቤት ሳይወጡ መንገድ ላይ ነኝ የሚሉ ጥቂት አይደሉም፡፡ የናታቸውን ቋንቋ መጠቀም የማይችሉና ስለጊዜ አጠቃቀም የማያውቁ ቁጥራቸው ብዙ ነው፡፡ ለማሰብና እራሱን ስነስርአት ለማስያስ የሚቸግረው ብዙ ሰንፍ ኢትዮጵያዊ ሞልቷል፡፡ ስለ ዲግሪያቸው አይነትና ብዛት ያወራሉ፡፡ ስለ ኢትዮጵያዊነት ያወራሉ፡፡ ኢትዮጵያ ተነሺ የምታወራው ግን ስለ ኢትዮጵያዊነት መሆን ብቻ ሳይሆን ሰው ስለመሆንም ጭምር ነው፡፡

ጥንት የተሰራውንም ሆነ ያልተሰራውን እያስታወሱ ያሁኑ ትውልድ ዋጋ እንዲከፍል የሚፈልጉም አሉ፡፡ ሰው ክፉ ሲሆን ያለፈውን እያስታወሰ መበቀል ይፈልጋል፡፡ ይህ የመጨረሻ አነስተኛና ኋላ ቀር አስተሳሰብ የተፈጠረው ሰወች በምክንያት ማሰብ ስለማይችሉና ትክክል መሆን ስለማይፈልጉ ብቻ ነው፡፡ ሰው አመዛዝኖ ሳይገባው ሲቀር ደግሞ የተሻለ ነገር ማሰብ ያቅተዋል፡፡ ምናልባት ይህንን ችግር ሁላችንም እናውቀዋለን፡፡ ዞሮ ዞሮ ግን ብዙ ኢትዮጵያዊ በምክንያት ለማሰብ ይቸግረዋል፡፡ ማለት የፈለኩት በርካታ ኢትዮጵያውያን አስተሳሰባቸውን ለትንሽም ነገር ቢሆን እውነት ለመናገር እራሳቸውን አላለማመዱትም፡፡ የዚህ አይነት ውሸቶችና ስህተቶች ተደምረው ለተጨማሪ ትልልቅ ስህተቶች በር ስለከፈቱ አሁን ብሄራዊ ችግሮች ናቸው፡፡ ስለ ድህነት፣ በሽታ፣ ወያኔ፣ ነጻነት ወዘተ ይወራል፡፡ እነዚህ ሁሉ ችግሮች ግን የተፈጠሩት ከአስተሳሰባችን መሆኑን ተረድቶ በራሱ ላይ እርምጃ የሚወስድ ጥቂት ነው፡፡ በምንኖርባት አለም ውስጥ የአስተሳሰብ ችሎታ በየጊዜው እያደገ ነው የሚሄደው፡፡ ብዙ ኢትዮጵያውያን ግን በአስተሳሰባቸው ላይ ከጊዜ ጋር ለውጥ አያሳዩም፡፡ ሰወች ስለሆን በሁሉም ነገር ፍጹም መሆን ባንችልም በብዙ ነገር ላይ ግን ትክክል መሆን ወይም መሻሻል ይቻላል፡፡ ኢትዮጵያዊው ግን የሚኖርበት ህይወትና ያለው ነገር በሙሉ ከአስተሳሰቡ የመነጨ መሆኑን ልብ አይለውም፡፡ ወይም አስተሳሰቡና ድርጊቱ የራሱና የወገኑ ህይወት ላይ ተጽዕኖ እንዳለው አያስተውልም፡፡

በምንኖርባት አለም ውስጥ የአስተሳሰብ ችሎታ በየጊዜው እያደገ ነው የሚሄደው፡፡ ብዙ ኢትዮጵያውያን ግን በአስተሳሰባቸው ላይ ከጊዜ ጋር ለውጥ አያሳዩም፡፡ ሰወች ስለሆን በሁሉም ነገር ፍጹም መሆን ባንችልም በብዙ ነገር ላይ ግን ትክክል መሆን ወይም መሻሻል ይቻላል፡፡

ካደጉ ሃገሮች መማር የምንችለው ብዙ ነገር አለ፡፡ ዋና ዋናወቹ ግን ባስተሳሰባቸው ጠንካራ፣ በአቋማቸው ቆራጥ ናቸው፡፡ ይህ ማለት በህይወታቸው አላማ አላቸው፡፡ ስህተታቸውን እንደ ውድቀት ሳይሆን እንደ ትምህርት ያዩታል፡፡ ይህ ማለት በየጊዜው መማርና ትክክል መሆን ይፈልጋሉ፡፡ ለውጥና ትርፍ ላይ ያተኩራሉ፡፡ ይህ ማለት ትኩረታቸው አድስ ነገር ለመፍጠርና ጠቃሚ ሆኖ ትርፍ ለማግኘት ነው፡፡ ጊዜና እቅዳቸውን በአንድ ላይ ያራምዳሉ፡፡ ይህ ማለት በእቅድ ስለሚያምኑ ያቀዱትን ነገር በጊዜው ጀምረው በጊዜው ለመጨረስ የቻሉትን ያህል ያደርጋሉ፡፡ ሃገራቸውንና ነጻነታቸውን ድርድር ውስጥ አያስገቡም፡፡ ይህ ማለት ስለሃገራቸውና ነጻነታቸው አዕምሮአቸውና ልባቸው አንድ ነው፡፡ በአስተሳሰባቸውና በአቋማቸው ጠንካራ ስለሆኑ ሌሎች ደካማ ሃገሮችን ታዛዥ ያደርጓቸዋል፡፡ ያለንባት አለም የምትሰራው እንደዚህ ነው፡፡ ይህ ማለት አሸናፊ ሁሉንም እንደሚያገኝ ጠንቅቀው ያውቁታል፡፡ የሚፎካከራቸውን ደግሞ ያከብሩታል ወይም ይወዳደሩታል፡፡ ይህንን ሁሉ የሚያደርጉት እንችላለን በሚለው ስለሚያምኑ እራሳቸውን በአስተሳሰባቸው ስላሳመኑትና ስሚሰሩ ብቻ ነው፡፡ ሌላ የተለየ ብዙ ሚስጥር የለም፡፡ ሚስጥርም ስላልሆነ ብዙውን ነገር ከዚህ መማር ይቻላል፡፡

ምንጭ - ታታሪ


23 views0 comments
bottom of page