top of page
  • Writer's pictureየመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ

ዝምታ ማለት ከማሰብ፣ ከማድረግና ከመናገር መቆጠብ ነው!



ዝምታ ማለት ከማሰብ፣ ከማድረግና ከመናገር መቆጠብ ነው!

ዝም ማለት፣ በአፍ ከመናገር መቆጠብ፣ መተውና ችላ ማለት ብቻ አይመስለኝም፡፡ ሰው አስፈላጊ የሆኑ ጉዳዮች ላይ በወቅቱ ሳይወስን፣ እርምጃ ሳይወስድና የሚደረገውን ነገር ሳያደርግ ወይም ሳይካፈል ሲቀር ዝም ብሏል ማለት ነው፡፡ እዚህ ጽሁፍ ላይ እነዚህ ሶስቱን ማለትም ዝምታ፣ መተውና ችላ ማለትን በአንድ ቃል ብቻ "ዝምታ" ብዬ እጠራቼዋለሁ፡፡ ሰው አስፈላጊ የሆኑ ጉዳዮች ላይ በወቅቱ ሳይወስን፣ እርምጃ ሳይወስድና የሚደረገውን ነገር ሳያደርግ ወይም ሳይካፈል ሲቀር ዝም ብሏል ማለት ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜም ሰው አሁን መወሰንና ማድረግ እንዳለበት ቢረዳም ለሌላ ጊዜ ያስተላልፋል፡፡ ታዲያ አንድ ሰው ከመወሰንና ከማድረግ የሚቆጠበው ለምድነው? ብለን ብንጠይቅ ምክንያቱ ብዙ አይደለም፡፡ ሰው የፈለገበት አላማ ላይ ለመድረስ ውጣ ውረድ ወይም ፈተና አለው፡፡ ከባድም ሆነ ቀላል መስዋዕት ያስከፍላል፡፡ እምነትና ድፍረት ያላቸው ግን እጅ አይሰጡም፡፡

ወስኖ ለማድረግ እምነትና ድፍረት በጣም አስፈላጊወች ናቸው፡፡ ድፍረት ስል ለሚደረገው ነገር አጀማመሩን፣ የስራው ሂደትና ሊሰጥ የሚችለውን ውጤት ደፍሮ እቅድ ማውጣት ወይም በውስጡ ተካፋይ ለመሆን ቁርጥ አድርጎ መወሰን ማለቴ ነው፡፡ እምነት ስል ደግሞ ጅምሩና የስራው ሂደት ውጤት ያስገኛል ብሎ ተግቶ በመስራት በራስ መተማመንና መድፈርም ጭምር ማለቴ ነው፡፡ ጥሩ ፍላጎትና ምኞት ማሳየት ለመልካም ነገር ስለሆነ በራሱ አይከፋም፡፡ ለመስራትና ውጤት ለማሳየት ግን እምነት፣ ድፍረትና መስራት ያስፈልጋል፡፡ ይህ ማለት ታዲያ ሰው ፍላጎቱን ለማሟላትና ምኞቱን ለማሳካት በእምነትና በድፍረት እየሰራ ውጤት ያስገኛል፡፡ እጅ አይሰጥም፡፡ እርምጃ ይወስዳል፡፡ ማድረግ አልችልም ብሎ እራሱን አይንቅም። ዝም አይልም ማለቴ ነው፡፡

ሰው የማድረግ ድፍረት ካዳበረ በምኞት ብቻ መኖር ስለማይፈልግና ዝም ስለማይል ከፍተኛ ውጤት ያፈራል፡፡ ምኞቱም ላመል ያህል ሳይሆን ለራሱና ለሃገሩ ወዘተ የሚጠቅም ነገር ለማድረግ በርትቶ ይሰራል፡፡ የጋራ ጉዳዮችም ላይ በተግባር ይተባበራል ለማለት ነው፡፡ ታዲያ የሰው ፍላጎትና ምኞት ምንድነው ብለው ሊጠይቁ ይችላሉ፡፡ ሰው ብዙ አይነት ፍላጎትና ምኞት አለው፡፡ ስለዛ ብዙ አልጽፍም፡፡ እኛ ኢትዮጵያውያንን በተመለከተ ግን ዋነኛውና ከብዙወቹ አንዱ የጋራ ፍላጎትና ምኞታችን ሃገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ ነጻነትና እኩልነት እንዲሰፍን እንፈልጋለን፡፡ እንመኛለን፡፡ ከላይ አርዕስቱ ላይ እንደጠቀስኩት ዝምታ፣ መተውንና ችላ ማለትን ቀንሰን በምትኩ ግን በቃ ካሁን በኋላ ለወገኔና ለሃገሬ ኢትዮጵያ ከእኩልነትና ከነጻነት ውጭ ሌላ ምርጫ የለም ብለን ቁርጥ አድርገን መወሰንና ነጻነታችንን ለማግኘት እርምጃ መውሰድ አለብን፡፡ ሌላ ምርጫ የለንም፡፡ በእያንዳንዳችን ውስጥ ያለውን እምነትና ድፍረታችንን አውጥተን መጠቀም ከቻልን ይህን የምንመኘውን ነጻነትና እኩልነት እውን ለማድረግ ደግሞ እንችላለን፡፡


66 views0 comments
bottom of page