top of page
  • Writer's pictureየመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ

ቀጠሮ፤ ቀጠሮ ማንነትን ማሳያ ትልቅ አጋጣሚ ነው!ቀጠሮ፤ ቀጠሮ ማንነትን ማሳያ ትልቅ አጋጣሚ ነው!

ቀጠሮ የሚያከብሩ ከሆነ ይህ ጽሁፍ እርስዎን አይመለከተዎትም፡፡ የበለጠ ለማዎቅ ከፈለጉ ግን አንብበው ሃሳብዎንም መስጠት ይችላሉ፡፡ ቀጠሮ የማያከብሩ ከሆነ ደግሞ ትንተናው ስለ እርስዎና ቀጠሮ ምንነት እንዲያውቁና እራስዎን እንዲገመግሙ ይረዳዎታል፡፡ ቀጠሮን ባለማክበር በተመለከተ እኛ ኢትዮጵያውያን በውጭው አለም እንኳን የታወቅን ነን፡፡ የአፍሪቃ ቀጠሮም ይባላል፡፡ አሁን ግን የኢትዮጵያዊው ቀጠሮ የሚባለውን ብቻ እናያለን፡፡ ለምን እኛ ኢትዮጵያውያን ቀጠሮ አናከብርም? ችግሩ ምንድነው? የቀጠሮን ምንንነት አናውቅ ይሆን? ለነዚህ ጥያቄወች መልስ ለመስጠት እሞክራለሁ፡፡ እንደሚመስለኝ በዙዎቻችን ቀጠሮን የምናየው ከምንገናኝበት ቦታና ሰዓት አኳያ ብቻ ነው፡፡ ቀጠሮ ግን ከቦታና ከሰዓት አልፎ ጠለቅ ያለ ነው፡፡ ቀጠሮ ከሰዓትና ከቦታም አልፎ ቁምነገርን፣ ክብርን፣ እቅድንና በቃል መገኘትን ይጨምራል፡፡ ነገር ግን ብዙዎቻችን ቀጠሮን አቅለን ስለምናየው እነዚህ አበይቶች አይታዩንም፡፡ ቢታዩንማ ኖሮ ቀጠሮ እናከብር ነበር፡፡

ቀጠሮ ማለት ክብርን፣ ማክበርን፣ እቅድን፣ በቃል መገኘትንና ማንነትን ማሳያ ትልቅ አጋጣሚ ነው፡፡ በቀጠሮ ምክንያት በህይወታችን ውስጥ ጠቃሚ የሆኑ ነገሮችን ልናጣ እንችላለን፡፡

ቀጠሮ ማለት ክብርን፣ ማክበርን፣ እቅድን፣ በቃል መገኘትንና ማንነትን ማሳያ ትልቅ አጋጣሚ ነው፡፡ በቀጠሮ ምክንያት ወዳጅ ጋር ልንቀያየም እንችላለን፡፡ በቀጠሮ ምክንያት በህይወታችን ውስጥ ጠቃሚ የሆኑ ነገሮችን ልናጣ እንችላለን፡፡ በቀጠሮ ምክንያት በሌሎች ዘንድ ላንከበር እንችላለን፡፡ የሚከተሉት ነጥቦች ከርስዎ ጋር ዝምድና አላቸው? ያለ በቂ ምክንያት ከዘገዩ ወይም እክል አጋጥሞዎት በጊዜው አለመድረስዎን ማሳወቂያ እድል ኖሮዎት መዘግየትዎን ካላሳዎቁ በራስዎ ላይ ቁጥጥር እንደሌለዎት ያመለክታል፡፡ ከዛም አልፎ ለራሳዎም ሆነ ለቀጠሩት ሰው ወይም ሰወች ክብር አያሳዩም ማለት ነው፡፡ ለተቃጠሩት ጉዳይም ክብዴት አይሰጡትም ወይም ደንታ የለዎትምና ባጋጣሚ እንደሚኖሩ ያመለክታል፡፡

በትንሿ ነገር ካልተለማመድን ነጻነትና እድገት መቼ እንገኛለን?

ባሉትና በቃልዎም ስለማይገኙ እንደ ሰነፍና ውሸታም ሊቆጠርብዎትም ይችላል፡፡ ስንፍናና ውሸት ሲደጋገም ደግሞ በውስጥዎ እንደ ልምድ ሆኖ ስለዳበረ ዘግይተውም ሲደርሱ ጥሩ እንደሰራ ሰው ፈገግ እያሉ ነው፡፡ ዘግይተው ሲደርሱም ወዲያውኑ ይቅርታ እንደማለት ተደባልቀው ቁጭ ይላሉ ወይም የሆነ ወሬ ይጀምራሉ፡፡ በሰዓቱ መምጣት ለፈረጆች ነው ብለው ተቀብለውታል፡፡ ለምን ዘገዬህ ተብለው ሲጠየቁ ክብርዎ የተነካ ይመስልዎትና ቆጣ ቆጣ ማለት ይጀምራሉ፡፡ ክብርዎ ግን የተነካው በራስዎ ገና ሲዘገዩ ነው፡፡ ወይም ለምን ተጠየቅሁ ብለው በውስጥዎ ብግን ይላሉ፡፡ ወይም በዚህ ወጥቶ በዚህ ወረደ እያሉ የውሸትም ሆነ የእውነት ምክንያት ይደረድራሉ፡፡ ይህንን እኔ በደንብ አይቻለሁ፡፡ ከሞላ ጎደል የዚህ አይነት ልምድ ካለብዎት በጣም ሊያሳስብዎት ይገባል!! መፍትሄው ግን ሁኔታውን ሰፋ አድርጎ በማየት ቀጠሮ ማለት ከሰዓትና ከቦታም አልፎ ቁምነገርን፣ ክብርን፣ እቅድንና በቃል መገኘትን መጨመሩን ማስታወስና ማወቅ ነው፡፡ እንዴት፣ መቼና በምን ወደ ቀጠሮ ቦታ እንደሚኬድም ማወቅ ያስፈልጋል፡፡ ቀጠሮ፤ እንደነሱ ናቸው? ቀጠሮ የሚያከብረውን ኢትዮጵያዊ ደግሞ ሰለጠንኩ ብለህ / ብለሽ ነው ወይ?’ የምንልም አለን፡፡ በርካታ ኢትዮጵያውያን በሰዓቱ መገኘት ማለት የፈረንጆች መሆኑን ባነጋገርም ሆነ በሃሳብ ደረጀ ከተቀበሉት ወደኋላ መሳቡን ዘ ተውታል።

ይህ የማሰብና የዕቅድ ማውጣት ጉዳይ እንጂ ሰዓት የማክበርን ባለቤትነት የወሰደ ዜጋ ወይም ዘር የለም፡፡ ከፈረንጅ ጋር ብቻ በምንቃጠር ጊዜ ቀጠሮን ማክበር እራስን እንደ ማታለል ይቆጠራል፡፡ ‘ፈረንጂ አትሁንብን/አትሁኝብን፥ ያበሻ ቀጠሮ እኮ ነው፥ ዝናብ ነበር፥ መጓጓዢያ ዘገዬ ወይም አልነበረም፣ ሰለጠንኩ ብለህ/ብለሽ ነው ወይ?’ ወዘተ በማለት ወቀሳና ሰበብ የምናባዛ ከሆነ ስለቀጠሮ ያለን ግንዛቤ እያነሰ እንጂ እየጨመረ አይሄድም፡፡ የሚደንቀው ሌላው ነገ ደግሞ እራሳችን ዘግይተን የቀጠርነው ግለሰብ በሰፊው ስላልጠበቀን ብቻ በራሳችን ጥፋት መቀየማችን ነው፡፡ ”አይ እሱማ/እሷማ ፈረንጅ ሆነው”፤ ”እስኪ አሁን ቆመው ቢጠብቁን ምናለበት”፤ ”ሰለጠንኩ ብሎ/ብላ ነው?” ብለን ቆጣ ቆጣ ማለት እንጀምራለን፡፡

ምክንያቱም ቀጠሮን የሚያከብር ግለሰብ፦

  • ለቀጠረው ግለሰብና ለራሱም ጭምር ክብር ያሳያል፡፡

  • በተቃጠረው ጉዳይ ላይ ክብደት መስጠቱንና አስፈላጊነቱንም ያሳያል፡፡

  • ጥንቁቅና ነገሮችን በዕቅድ የሚሰራ መሆኑን በተግባር ያሳያል፡፡

ስለዚህ በሚቀጥለው ጊዜ ቀጠሮ ሲኖረን ከላይ የተጠቀሱትን ነጥቦች ብናስብባቸው አይከፋም፡፡

ቀጠሮ አክባሪውን ኢትዮጵያዊ ደግሞ የምናደንቅና የጠቀምን መስሎን፤ ”እከሌማ ልክ እንደነሱ ነው/ናት! (እንደ ፈረንጆቹ)” እንላለን፡፡ በኛ አባባል ያ ግለሰብ እራሱን መሆን አይችልም ማለት ነው? ቀጠሮን በተመለከተ የኛ ነገር በከፊል ይህንን ይመስላል፡፡ በህይዎታችን ውስጥ በርካታ ጉዳዬች በቀጠሮ አማካኝነት የሚፈፀሙ ናቸው፡፡ ምክንያቱም “ቀጠሮ በተለያዩ የሕይወታችን ዘርፎች ውስጥ ሰፋ ያለ ድርሻ አለው፡፡” ስለዚህ ቀጠሮ አለማክበራችንና ትችታችን ወደኋላ ለመቅረታችንም አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡ አብዛኛዎቻችን ኢትዮጵያዊያን በህይወታችን ውስጥ አንገብጋቢ የሆኑ ጉዳዮችን እንደ ተራ ነገር ማየት የለብንም፡፡ ከነዚህም ውስጥ አንዱ ቀጠሮን በተመለከተ ነው፡፡

ምንጭ - ታታሪ


20 views0 comments
bottom of page