top of page
  • Writer's pictureየመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ

"ማንነት ከሞላ ጎደል" ማን ነኝ ብለው ያውቃሉ?



"ማንነት ከሞላ ጎደል" ማን ነኝ ብለው ያውቃሉ?

በህይወት ላይ አርኪና ተቀባይነት ያለውን ነገር ለማድረግ ብዙ ቀላልና ከባድ ነገሮች ሂሳብ ውስጥ ይገባሉ፡፡ ታዲያ እንዳው አልፎ አልፎ እኔ ማነኝ? የማደርጋቸውን ነገሮች የምጠቀምበት ስልት ምን ይመስላል? ምን እያደረኩ ነው? ብለው እራስዎን ጠይቀው ያውቃሉ? ማን ነዎት? የዚህ አርዕስት አላማ እርስዎ ሰው እንደመሆንዎ መጠን በነገሮች ላይ ያለዎት አስተሳሰብና ድርጊት ምን እንደሆነ መርምረው እራስዎ እንዲደርሱበት ፍንጭ ለማሳየት ነው፡፡ እርስዎ በራስዎ ማንነትዎን በሚያስቡትና በሚያደርጉት ነገር መሰረት በማድረግ ማን እንደሆኑ በራስዎ እራስዎን እንዲጠይቁ ታስቦ ነው፡፡ እነዚህ አስተሳሰቦችና ድርጊቶች ህይወት ላይ ከፍተኛ ቁርኝት ስላለቸው ከታች የተጠቀሱትን ነጥቦች ሲያነቡ አረፍ እያሉ እንዲያስቡበት እጠይቃለሁ፡፡

የተጠቀሱት ነጥቦች ቀላልና በቀላሉ የሚታለፉ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ዋናው ቁምነገር ግን ቀላሎቹ ነገሮች በሚከሰቱ ጊዜ በትክክልና በተገቢው ካልተደረጉ በቂ ልምምድ ስለማይኖር ከፍ ያለ ቁምነገር ለማድረግ ያዳግታል፡፡ አንዳድ ሰዎች ከበሉና ከጠጡ፣ ስራም እንደነገሩ ሰርተው ከተመልሱ፣ ከዛም ባገኟት ገንዘብ ለምግብ፣ ለልብስ፣ ለቤተሰብ፣ ለቤትና ለመሳሰሉት ከበቃቸው ህይዎት ከዛ በልይ መሆኗን ይዘነጋሉ፡፡ ለማለት የፈለኩት ታስቦበትም ይሁን ባጋጣሚ የሰው ልጅ በተቻለ መጠን ህይወት ውስጥ በሚከሰቱ ነገሮች ላይ ተገቢውን ውሳኔ መወሰንና ማድረግ አለበት፡፡ አይ ይቺማ ምን አላት ብሎ ማለፍና መናቅም እንደ እጅ መስጠት ሊቆጠር ይችላል፡፡ እርስዎም እንደሚያውቁት ሰው ፍጹም አይደለም፡፡ ሆኖም ደግሞ ከዚህ በታች የተጠቀሱት ነጥቦች በተቃራኒው ከተደረጉ ቢያንስ ህይወት እንዲጥምና እርካታ እንዲኖረው አስተዋጽኦ ያደርጋሉ፡፡

  • ለቀጠሮ ቁርጥ አድርጎ ወዲያውኑ ቀጠሮ እንደመያዝ እንደዋወል ይላሉ?

  • ባጋጣሚ በቀጠሮ ዘግይተው የት እዳሉና መቼ እንደሚደርሱ ከመናገር ይልቅ እየመጣሁ ነው ይላሉ?

  • ሲያዳምጡ፣ ሲናገሩና ሲያስቡ ፊትዎ ይቋጠራል?

  • ሃሳቦች ሲቀርቡ በአፍራሽነት መልኩ ግን ማለት ያበዛሉ?

  • ሳያጣሩ በሃሜት አምነው ይወስናሉ?

  • ሻይ ቤት ውስጥ ተቀምጠው ለበርካታ ሰዓታት በወሬ ጊዜዎን ያባክናሉ?

  • ስለ ሌላ ሰው ማውራትና ማማት ያዘወትራሉ?

  • ስራዎን ለደመወዝ ነው ብለው ያስባሉ?

  • ጓዴኛ ወይም የቅርብ ቤተስብ ጋር በተደጋጋሚ ይጨቃጨቃሉ?

  • ለሚስትዎ ወይም ለባልዎ ታማኝ አይደሉም?

  • ለትንሽም ሆነ ትልቅ የሚደረግ ነገር ላይ እጅ ይሰጣሉ?

  • ኢትዮጵያዊ ሆነው ከልብ ኢትዮጵያዊነት አይሰማዎትም?

  • ጥራት ያለው ነገር ሲያዩ ወይም ተካፋይ ሲሆኑ አያደንቁም?

  • ቶሎ ቱግ ብለው ይናደዳሉ?

  • የሆነ ነገር ለማድረግ ይህንን አልችልም ብለው ችሎታዎን ባጭሩ ይገቱታል?

  • ሲጋራ ያጨሳሉ? ጫት ይቅማሉ?

  • በየአጋጣሚው ከልክ በላይ ይጠጣሉ? ጠጥተውስ መኪና ይነዳሉ?

  • ገንዘብና ቁሳቁስ ደስታ የሚሰጥ ይመስልዎታል?

  • ጓደኞችዎን ወይም የሚያውቋቸውን የሚያስታውሷቸው እርስዎ እርዳታ ሲፈልጉ ብቻ ነው?

  • እከሌ ወይም የሚጠላኝ ሰው አለ ብለው እራስዎን ይጠራጠራሉ?

  • ብዙውን ጊዜ እርካሽ ነገር ከሱቅ ይገዛሉ?

  • በቀላሉ መደሰት ጥሩ ቢሆንም ይረካሉ?

  • አጥፍተው ይቅርታ አይጠይቁም? ወይም ሳያጠፉ በፍራቻ ወይም በይሉኝታ ይቅርታ ይጠይቃሉ?

  • ማንነትዎን ደብቀው ያለምንም ምክንያት ኢሜል ይልካሉ? ፈሪ ነዎት?

  • ሰልፍ ላይ ተራዎን ሳይጠብቁ ወይም ቀድመው ሳይመጡ ዘው ብለው መስተንግዶ ይፈልጋሉ?

  • ዝግጅት ኖሮዎት ማስታወቂያ ሲያዎጡ አድራሻ፣ ሰዓትና ዋጋ ይረሳሉ ወይም ይደብቃሉ?

  • ለቅርብ ጓደኞችዎም ቢሆን በጅምላ እንኳን አደረሳችሁ ብለው SMS ይልካሉ?

  • ነጻ አይደለሁም ብለው ካሰቡ ነጻ ለመሆን እርምጃ አልወሰዱም?

  • ነጻ ነኝ ብለው ካመኑስ ነጻነትዎን ለራስዎ ብቻ ይዘው ዝም ብለው ቁጭ ብለዋል?

ምንጭ - ታታሪው


15 views0 comments
bottom of page