top of page
  • Writer's pictureየመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ

የእጆቻችን አራት ጣቶች የአቅጣጫ አመለካከትና የኛ አመለካከት (በሰሙ ቢንት ሽፋ)

Updated: Jun 9, 2019



የእጆቻችን አራት ጣቶች የአቅጣጫ አመለካከትና የኛ አመለካከት

ብዙ ጊዜ በአብዛኞቻችን ዘንድ ይህ ከላይ በርእሱ የገለፅኩት ነገር ይስተዋላል ። እሱም… በእጆቻችን አራት ጣቶች መካከል አቅጣጫ ጠቋሚ ጣታችንን ብንመለከት አቅጣጫ ጠቋሚ ጣታችን ሁሌም ሰዎችም ላይ ይሁን አቅጣጫዎች ላይ ያ… ብሎ ሲጠቁመን እኛም ትኩረታችንንና አመለካከታችን ሙሉ በሙሉ አቅጣጫ ጠቋሚ ጣታችን ላይ እናሳርፈዋለን። ሌሎች ሶስት ጣቶቻችን ግን ወዴትና በማን ላይ እንደሚያመለክቱ አስበነውም ይሁን ተገንዝበነው በፍፁም አናውቅም ። ምክንያቱም ትኩረታችን እዚያ… ያ… ብሎ ወደ ሌላ አቅጣጫ ያሳየንን ጣታችን ብቻ ላይ ስለምናደርግ ብዙ ጊዜ እኛ ሰዎች የሌሎችን ጥሩም ይሁን መጥፎ ተግባራት አጉልተን ስለምንመለከት የራሳችንን ጥሩም ሆነ መጥፎ ስራዎች ትኩረት ሰጥተን አናውቅም። ዘውትር የሰዎች መልካምም ይሁን መጥፎ ተግባራት በመከታተል ስለምንጠመድ ወይም ጊዜያችንን ከሌሎች አይን ውስጥ ጉድፍ በማውጣት ብቻ ስለምናባክን የራሳችንን እልፍ ጥፋትና ችግርን የማየት እድሉ አይገጥመንም። እኔ ማነኝ ? ከማለት ይልቅ እሱ ማነውን ? እናስቀድማለን ። ያለንን በስርአቱ ከመጠቀም ይልቅ የሌላውን የኔ ባደረገው በሚል ምኞት ተጠምደን እንገኛለን ። ፊት ለፊታችን ያለውን ከማየት ይልቅ እሩቅ ያለው ያጓጓናል። እኛነታችን በደንብ ሳንመለከት ሌሎች ጥቂት ጥፋት ካለባቸው አግዝፈን የእነርሱን በቻ እንመለከታለን ።

እራሳችን የበላይ እያደረግን ሌሎች የበታች አድርገን እንመለከታለን ። ኧረ ጭራሽ አንዳንዶቻችን በፍፁም እኔ ማነኝ ብለን እራሳችን ጠይቀን አናውቅም ። ሌሎች ችግር ሲገጥማቸው ለችግራቸው መፈትሔ ከመፈለግ ይልቅ እገሌ እኮ ችግር ገጠመው ብለን የቡና ቁርስ እናደርገዋለን ። የራሷ አሮባት የሰው ታማስላለች አይነት ነገር ነው !! መቼም ከማውራት መርዳት የሚቀል ይመስለኛል ። ችግረኛውን በአካልም ካገኘነው አይዞህ /ሽ ከማለት ይልቅ ልክ ከላይ ርእሱ ላይ እንዳስቀመጥኩት አቅጣጫ ጠቋሚዋ ጣታችን ችግርኛው ላይ እንቀስራለን። ሶስቱ ጣቶቻችን እኛ ላይ እንደሚቀስሩ ዘንግተን !

  • ያ…ማነው ? ከማለት ይልቅ እኔ ማነኝ ? ብለን እናውቃለን ?

  • እገሌና እነእገሌ እንዲ ሰሩ ከማለት ይልቅ እኛ እንዲህ ሰራን ወይም መስራት አለብን ብለን እናውቃለን ?

  • የሌሎች መጥፎ ስራዎች ከማግዘፍ የኛ መጥፎ ተግባሮች ታይቶን ያውቃል ? አያውቅም !

ምክንያቱም የኛ ትኩረት በዛ በአቅጣጫ ጠቋሚው ጣት ተመርዟል። እኛነታችን እየወደቅን ሳይመስለን የሌሎች ውድቀት ስናይ እንሳለቃለን። በኛ ውስጥ ያሉ መልካም ነገሮች ለሌሎች የሚጠቅሙ ከሆነ ለምን ጥቅም ላይ አናውለውም ? እናውለው እንጂ “መልካም መሆን ለራስ ነው” አይደል የሚባለው ? ይህ ነገር አለኝ ይቀመጥ ነገ እስራዋለሁ ሳይሆን ማለት ያለብን ሰርተን ለመልካም እናውለው። መልካም ለመሆን ደግሞ የጊዜ ገደብ አያስፈልገውም። መጥፎነትም ከራስ ለማላቀቅ ልክ እንደዛሬው። ምክንያቱም “ጊዜ ታክሲ አይደለም ቆሞ አይጠብቀንና”። ደግሞ በምንና መቼ እንዴት እንደምንሞት አናውቅም። የእኛ ነፍስ ያለችው በፈጣሪያችን እጅ ስለሆነች እናም ወዳጄ ሁሌም አንድ ወደ ሌላ መጥፎ ነገር የሚመራህን ሳይሆን መከተል ያለብህ ብዙ ሆነው ወደ መልካም የሚጠሩህን ተከተል ። እርሱ ማን ነውን ትተን እኔ ማን ነኝን እናስቀድም ።

ተጻፈ - በሰሙ ቢንት ሽፋ (semu bint shifa)


21 views0 comments
bottom of page