የመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ
"በጠራ ጨረቃ"

በጠራ ጨረቃ በእኩለ ሌሊት አይኖቿ እያበሩ እንደ ከዋክብት «ሳማት ! ሳማት !» አሉት «እቀፍ ! እቀፋት።» አላወላወለም ወጣቱ ታዘዘ ወገቧን አንገቷን እጇን በእጁ ያዘ ምንም እንኳ ጡቷ እንደሾህ ቢዋጋ ጣቷ በመሆኑ የጉማሬ አለንጋ ጆሮ ግንዱን ሰማው በጥፊ ሲናጋ። ዋ ጀማሪ መሆን ! ዋ ተማሪነት ዋ ትእዛዝ መፈጸም ዋ ምክር መስማት ! በጠራ ጨረቃ በኩለ ሌሊት...
/መንግስቱ ለማ /