top of page
  • Writer's pictureየመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ

ወፍዬ... ወፊቷ (አብዲ ሰዒድ)


ወፍዬ... ወፊቷ (አብዲ ሰዒድ)

ዛፍተጥሏል አሉኝ ማዶ ከዚያ መንደር

ጉዞ ጀምሬያለሁ ማገዶ ልበደር።

መንደርተኛው ሁሉ መጥረቢያውን ታጥቆ

ግንድ ይሸነሽናል ሥሩን ሰነጣጥቆ።

ፍልጡስ ይጠቅመናል ግዴለም ፍለጡ

ግን አደራችሁን ችግኝ አትርገጡ።

ቡቃያውም ይዟል አምሮበታል ሰብሉ

ምነው ባያረግፉት ወፎች እየበሉ።

ወፍዬ... ወፊቱ

ወፍዬ... ወፊቱየ

የታደልሽ ፍጥረት ባለጸጋይቱ።

አታርሺ አትዘሪ

ፍቅርነሽ ስትዞሪ

ማንስ ይከስሻል አገዳ ብትሰብሪ።

እኔስ አልዘረጋም፣ ወንጭፌን ጨክኜ

የደም ጎጆ አልሰራም፣ ጠጠር አባክኜ።

ይድላት ትፈንጭበት፣ ያውላት እርሻዬ

የተረፈው ይበቃል፣ አይጠፋም ድርሻዬ

ወፍዬን አትንካት፣ በል ተዋት ባሻዬ።

አንዳንዴ ደግ ነው፣ አንዳንዴም ይከፋል

የቀበሌው ባሻ፣ ያለማል ያጠፋል።

ዝንጉርጉር ነው ሆዱ፣ አይለይም መልኩ

ይጠባል ይሰፋል፣ አይታወቅ ልኩ

ለወፍ ይታጠቃል፣ ጀግና ነው ምትኩ።

ወፍዬ... ወፊቷ

ወፍዬ... ወፊቷ

አልጠረጠርሽም ወይ ልበ መልካሚቷ።

ባታርሺ... ባትዘሪ

ፍቅር... ብትዘምሪ

አይተዉሽም... እኮ ተይ አትዳፈሪ።


አብዲ ሰዒድ

32 views0 comments

Recent Posts

See All
bottom of page