top of page
  • Writer's pictureየመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ

ቱፍ !! (ጃዊሳው- ዓሊ )


ቱፍ  !! (ጃዊሳው- ዓሊ )

የተማረውሻ ! ባለ - ከረባቱ ባለ - ኮፍያው !

ሲጭኑት አይጮህም ልክ እንደ - አህያው

ጎረቤቱ ሲጮህ ! በእሳት እየጋየ

በጆሮው እየሰማ በዐይኖቹ እያየ

ከጌቶቹ ግቢ እማይደርስ መስሎት

ጭራውንይቆላል በጊዜያዊ ምቾት ::

የተማረ ውሻ ! ባለ - ከረባቱ !

ባለ - ነጭ ሸሚዝ ! ባለ - ጥቁር ሡሪ !

ለሄደው ለመጣው ተጎንብሶ እዳሪ !!

ብለውእየጠሩት ክፍንችላ ቡቺ ቦሬላላሬቦ !

የሰው ደም ጠጥቶ ቅንጥብጥቢ ጠግቦ

ከግር ሥር ይተኛል ጌቶቹን አጅቦ ::

የተማረ ውሻ !!

ይሄ ቡቺ-ቡቺ ሆድ አደሩ እንከፍ !

ካፊያ ሲነካካው ጭሪውን መቆለፍ !

በጠራራው ፀሀይ ምላሱን መዘርገፍ !

በጭራሽ ! አይተውም !!

ከጌታው ጫማ ስር ተኝቶ ማንኳረፍ ::

ቱፍ !!

የተማረ ውሻ ::

እ - ኢ- አ / 1993 / ጃዊሳው ( ዓሊ )

45 views0 comments

Recent Posts

See All
bottom of page