top of page
  • Writer's pictureየመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ

. . . በሬው! . . . (አብዲ ሰዒድ)


. . . በሬው! . . .  (አብዲ ሰዒድ)

እዩት ያንን በሬ በቀንዱ ተማምኖ

ያሸብረን ይዟልላሞች ላይ ጀግኖ

ላሞች እንደሆኑመጠቃት ልምዳቸው

ወተት እንዲያጠጡኮርማ ነው ግዳቸው።

በሬ እየሸለለ፣በሬ እየፎከረ

በሬው እያጓራ፣ስንቱ ደጅ አደረ፤

ይወጋል ይረግጣል፣

ሲሻው ያንሳፍፋል

በሬ ሆይ አይምሬው፣ ትውልድ ያጣድፋል።

ተው በሬ … ተው ኮርማ

እባክህ ተመከር፣ ያገር ምክር ስማ

ተጥለህ እንዳናይህ፣ ከቄራው አውድማ።

የሚሮጥ፣ የሚሸሽ፣ የሚበረግገው፣

ቀንድህን በመፍራት፣ የሚያደገድገው፣

ገና ብቅ ስትል መንገድ የሚጠርገው ᎐᎐᎐

ይሄ ሁሉ ፈሪ፣ ይህ ሁሉ ቦቅቧቃ

ከዘመን ፍራቻው፣ ሲባንን ሲነቃ

ሆ! ያለብህ እንደሁ ታጥቆ በቆንጨራ

ያዝ ያለህ እንደሆን ከቦ በገጀራ

ማምለጫም አይኖርህ ለአንገትህ ካራ።

“በሬ ሆይይ በሬ ሆይይ

ሳሩን አየህና ገደሉን ሳታይ

መግባትህ ነው ወይይይይ”

ብለን እንዳናለቅስ ቆዳህን ሲገፉ

ዛሬን አታስጀግር ተው ሰዎች ይለፉ

በሰላም፣ በጤና፣ በፍቅር ይረፉ

ላንተም አይበጅህም፣ ያጠፋሃል ግፉ።


አብዲ ሰዒድ

19 views0 comments

Recent Posts

See All
bottom of page