top of page
  • Writer's pictureየመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ

የሼህ ሁሴን ጅብሪል ትንቢታዊ ግጥሞች (ክፍል -05)



24. ጦሩን አስከትሎ መተማ ሲደርስ

ከበቅሎው ወረደ አጼ ዮሐንስ

የጦሩን መከታ ጋሻውን ሊለብስ

እሱ እራሱን አጥቶ ሰውን ሊያስጨርስ

በጥረት አይድንም ጥፋ ያለው ነፍስ::

25. እንዴት በገዛ እጁ ሞት ይመኛል ሰው?

መተማ አትሂድ ብዬ ብመክረው

መቸ ይመለሳል ያዘዘበት ሰው

(ደም እየሸተተው ሞት እየጠራው

እንዴት ሰው ለአንገቱ አያዝንም ወይ ሰው)

26. ፈረሱን ጫጭነው ድርቡሾች ዘለቁ

ኸሊፋና ዑመር ድባጢን ዘለቁ

ከዚያም ከዚህ ያሉት ተደበላለቁ

ዮሐንስ ከጭፍራው ፈርተው ተጨነቁ

የሚያስታርቅ ጠፍቶ ስንት ሰው አለቁ::

27. የአህያ ልጅ በቅሎ በብር ተሸልማ

ዮሐንስን ይዛ ወረደች መተማ

ከጌታዋ ራስ ጋር በቁም ልትቀማ

ስንቱን ሰው ፈረጀው ደጉ አገር መተማ

ስንቱን አርዶት ነበር እስላም እንዳይለማ::

28. ምኒልክ ደስ አለው ምጡን ሲፈረጅ

እኔም ጫት በመቃም ነጀ ወጣሁ እንጅ

እስላምን የሚወድ ወደፊት ይምጣ እንጅ

ዮሐንስ ክፉ ነው የለውም ወዳጅ

መተማ ደጉ አገር ገላገለን እንጅ::

አላህ ገላገለን በዟሂር መከራ

እንግዲህ ምኒልክ አይዞህ እንዳትፈራ

ዮሐንስ ሊሄድ ነው ጦሩን እየመራ

ማረድ የለመደ መቼም ሞት አይፈራ::

ሞቱ ብላሽ ሆነ እንዲህ ሲንጠራራ::

29. አንተም ጨካኝ ነበርክ ጨካኝ ወረደብህ

እንደ ፍሪዳ ላም በቁምህ አረዱህ

በቅሎና ገጧ ጋር በቁሟ ማረኩህ

እራስክን ቋንጣ አርገው ሥዕል አደረጉህ

አላፊው አግዳሚው እንዲሰደድብህ::


42 views0 comments

Recent Posts

See All
bottom of page