• የመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ

የሼህ ሁሴን ጅብሪል ትንቢታዊ ግጥሞች (ክፍል - 06)30. አልሐምዱሊላሂ ለዚህ አበቃህ

ዮሐንስ እራስህን በችንካር መቱህ

አላፊው አግዳሚው እስቲተፋብህ

ሰው የጁን አያጣም እንዲህ አረጉህ

የወሎን መሻኢህ እያረድክ ሰቅለህ::

31. አጠቋቆራቸው ከሰል ይመስላሉ

ከመሕሉቁ ብሰው በጣም ይጠቁራሉ

መተማን ድል አርገው ጎንደር ይገባሉ

ደቆራና ዳይንት ብዙ ሰው ያርዳሉ

ከሺህ ታቦት በላይ በእሳት ያነዳሉ::

32. ማረድ ተጀምሮ ድራና ፎገራ

ምን ይበጀው ይሆን የጎንደር አማራ?

አይተኸው የማታውቅ መጣብህ መከራ

ብዙ ሰው ይጠፋል ካልሰለመ አማራ

ይለበልበዋል ያርደዋል በካራ::

33. ወደ ሱዳን አገር ዋሪዳው ካመራ

ደፈረኝ ካልሉ ሳዳቶችን ልጥራ

አሁን ድረሱልኝ ይዞኛል ደብተራ

ወትሮም የመሐዲ ዘር አስላችሁ አይኮራ

ገላገላችሁኝ አልቅሼ ብጣራ::

34. ቢደፍሯቸው እዳ ዝም ብል ችግር

ዋሪዳው መጣና አለኝ ተናገር፣

እንግሊዝ ከሱዳን ካልለቀቀ አገር

ይዘገያል እንጅ ኋላ አለ ነገር

መሕዲ ዘር ባለቃ ሲል ደንገር ደንገር::

ሱዳን ብሎ ማለት ተፍሲሩ ሻንቅላ

(ከነሱ ካልሆነ አይጋቡም ሌላ

መጠጥ ይወዳሉ ሐራራም አይጠላ)

ዘራቸው ልዩ ነው ናቸው የአላህ ሰባት በላ

ሰባት ቋንቋ አላቸው ሁሉም በጠቅላላ::

35. የሱዳንን ነገር በስንቱ ላውሳቸው

ካላስፈነደዱ ፈርጅም አይመስላቸው

ከእኛም ሰው አይተፋ ነጭ ያስተማራቸው

የወንዱስ መላ አልቋል ሴቱ አላህ ያብጀው

ስንቡል እያጠበች ገልባ ከሰጠችው::

36. ድርቡሽና ሱዳን መልካቸው ጥቁር ነው

አገሩ አንድ ቢሆን ቋንቋው እየቅል ነው

ጥንቱም ፍጥረታቸው ዘራቸው ልዩ ነው

በዟሂር ሲጠሩ ስማቸው እስላም ነው

ቸርነት አያጡም እጃቸው ለጋስ ነው::

37. ድርቡሽ ጥሩ እስላም ልባቸው የጠራ

ሶላትን አይተውም ቢበዛበት ሥራ

ችግርም ቢገጥመው ይችላል መከራ

አገራቸው ሜዳ የለውም ተራራ

ልብሳቸው ቀሚስ ነው የለውም ዳኢም ታጥቀው ሥራ::


19 views0 comments

Copyright © 2018 Meskan Media Network - All Rights Reserved. E-mail : meskanmedia@gmail.com

  • YouTube - White Circle
  • White Spotify Icon
  • White Apple Music Icon
  • White Amazon Icon
  • White Facebook Icon
  • Twitter Clean