top of page
  • Writer's pictureየመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ

የሼህ ሁሴን ጅብሪል ትንቢታዊ ግጥሞች (ክፍል - 10)



62. አባቱ (መተማ) ሄዶ አፈር ሊቀምስ

ልጁ ኋላ ቀርቶ መስሎት የሚነግሥ

እንኳን የልጅ ልጁ እራሱም አይነግሥ

በአዙል ተፈርዷል ምኒልክ ሊነግሥ

አስቦ ነበረ በሁለት ሊነግሥ::

63. እኔ በሚካኤል ደንግጨ አልታመም

ኢልሙም ከንቱ ይሁን የቀረው ዘላዓለም

እንዲህ ሊያጋልጠው ዲኑንም ሊዘ(ዞ)ልም

ነግሬው ነበረ ግን ነገሬ አይጥምም፣

አውጥቻለሁ ጣሉ ይህ አህያ አይድንም::

64. ምኒልክ አሥመራን ለነጭ ከሸጣት

ይዘገያል እንጅ ይመጣል ፍጅት፣

ስንቱ ይዋረዳል ከወንድም ከሴት

ሸዋ የዚያን ጊዜ የለውም ዕረፍት

ቀጥሎ ይነዳል የጀርባው እሳት::

65. እንኳን ለኢያሱና ሳይታይ አባቱ

ምን ብለናት ነብር ትመስክር እናቱ

እስከሚሞት ድረስ ኋላ ባሟሟቱ፣

ደግሞ አጼ ዮሐንስ መተማ ሳይዘምቱ

ትዝ አይላችሁም ወይ በጫት የማልኩቱ::

66. ክፉ ዱላ አለን የማይምር ለዕለት

እስተውሎ የሚመታ በሩቅ የማይስት

እኔ ሹም አልፈራም ጉድ ካየሁበት

እንዴት ጥንብ ሰጡኝ አያውቅም መስሎት

ማነው ያሳሳተው ያደለው እሳት።

67. ሰክሮ ካልወደቀ አያራም ከቤት

ዛፍ ካልተቆረጠ አይወድቅም እመሬት

ሴት ፈርጇን ካልሠፋች የባሏን ንብረት፣

እያሱ አደብ ግዛ እንዳትሳሳት

ቆጥረህ ድረስበት መነን ምንህ ናት?

68. ሚካኤል ተው ተብት በኩፍር ሳትቀጣ

ይበቃሃል የሚል ከአላህ አዋጅ መጣ

እንዴት ያለች ንፋስ የሆነች ባላንጣ

በጥፊ ብትመታው በአፍንጫው ደም መጣ

ጉዞው ተቃረበ እሩሁ ልትወጣ::

69. ጉግሣና ራስ (ወ)ሎሌ፣ አጼ ዮሐንስ

ሚካኤል፣ ምኒልክና አጼ ቴዎድሮስ

ዘውዲቱና ፈረንጅ ተፈሪ ድረስ

በብልሃት ገዟት አልጋው እንዳይፈርስ

መጨረሻው ከፍቶ ጣሉት እንደርኩስ::

70. የአላህን ትተው በውሻ የሚመሩ

በሐበሻ መሬት ግፍን የሚሠሩ

ቁመታቸው አጭር መልካቸው የሚያምሩ

አይነግሡም ብላችሁ አትወዳደሩ

ሃምሳ ዓመት ይነግሣል እግረ ውትርትሩ::

71. ባሕር ወዲያ ማዶ ዘር መጣ ሊጠቅም

ግድግዳው የሚያምር በሽንጥ የሚጠቅም

ቅጠሉ ለስላሳ ቁመቱ ረዣዥም

እሱን ያልተከለ እንዴት ይለጅም

ሸዋ በተለየ ያለሱ አይቆምም::


77 views0 comments

Recent Posts

See All
bottom of page