top of page
  • Writer's pictureየመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ

የሼህ ሁሴን ጅብሪል ግጥሞች (ክፍል - 23 እና የመጨረሻ)



214. እንኳን ያ(የ)ለው ሰው ጥቂት ልጅነት

ሽማግሌ ባልቴት በምርኩዝ በከብት::

215. ጡሩንባውን ነፍቶ አዋጅ ያደርግና


ወንዱንና ሴቱን ክተት ይልና

በመድፍ በመትረየስ ያንደቀድቅና

ይቆላዋል ከዚያ መኻል ያደርግና::


216. አዋጅ ሊደረግ ሲሉ ክተት

የራሕመት ደመና ያጠለለለት

ማቄን ጨርቄን ሳይል አውድማ ክትት

ባቄላ ፍሬ አለች ዲቃን የሚሏት

ስትቀቀል ውላ ፍላት አይነካት

ከርብ መከራ ጌታ የሚያወጣት፣

አንድ ሺህ ሦስት መቶ ከዘጠና ውስጥ

አራት መቶ ሳይሆን እዚያ ውስጥ ናት

የፍጥረቱ አውድማ እርብ የሚሏት::


217. የርብን መከራ ስንቱን ልንገርህ

ቂያማ ቀን ይመስላልገና ሲቀርብህ

ኸልቁ ይሸበራል እንደ ቂያማ ዕለት

ቀኗንም ወራቷንም ከዋሸንላችሁ

እንዳትሄዱ አደራ የእኛ የሆናቸሁ

የራሕመት ደመና ሽፍን ያድርጋችሁ::


218. ነቢ ተናግረዋል ኸይረል በርያት

ክፉ ነፋስ አለች ሐበሻ መሬት

ኸልቁን የምትጨርስ ቀንና ሌሊት

ማእናውን ልንገርህ ንፋስ ያልንበት

ሽብርና ጭንቀት የበዛባት ናት

እጦሩ መካከል አለ አሉ ድንገት::


219. ከርብ ጦርነት ወዲያ ያለቸው ሰዓት

ክብረትና አፊ(ሠ)ያ ናት ደስታ ውበት

ምናልባት ብትተርፍ ከሰዎች ጥቂት::


220. ጥሩም በሽታውም መከራው ብዛት

ይበቃል ነበረ የአንድ ማሳ እሸት

አላህ ላደረሰው በዚያች ዘመናት

አባክህ አድርሰን እረቢል (ግ)አዘት::


221. አዱኛ ደኅና ሁኚ ጋሰብኩሽ

ምስክሬ አንቺ ነሽ አዋጅ እንዳትረሽ::

35 views0 comments

Recent Posts

See All
bottom of page